Connect with us

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በትርፍ ተንበሸበሹ

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በትርፍ ተንበሸበሹ
ምንጭ፡- ወንድአፍራሽ አሰፋ - የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

ዜና

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በትርፍ ተንበሸበሹ

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በትርፍ ተንበሸበሹ

      በ2013 በጀት የመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት ከታክስ በፊት ብር 8 ነጥብ 48 ቢሊዮን አትርፈዋል፣

      ልማት ባንክ ከኪሳራ ተላቋል፣

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር በፋይናንስ ዘርፍ የሚገኙ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2013 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በጊዚያዊ የሂሳብ መረጃ መሠረት ከታክስ በፊት በድምሩ  8 ነጥብ 48 ቢሊዮን ብር አተረፉ፡፡ 

ይህ አፈጻጸም የልማት ድርጅቶቹ አቅደውት ከነበረው የብር 10 ነጥብ 31 ቢሊዮን ትርፍ አንጻር ሲታይ ክንውናቸው ከዕቅዳቸው 82 ነጥብ 26 በመቶ እንደሆነ የድርጅቶቹ አፈጻጸም የካቲት 5 እና 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ታውቋል፡፡

የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን፣ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል ናቸው፡፡ የካቲት 12 ቀን 2013 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አፈጻጸሞች በተገመገሙበት ወቅት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ መድረኩን መርተዋል፡፡ 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ የየልማት ድርጅቶቹ የቦርድ ተወካዮች፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የማኔጅመንት አባላትና እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የኤጀንሲው ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በግምገማው ተሳትፈዋል፡፡

ድርጅቶቹ ይህንን ትርፍ ሊያገኙ የቻሉት የባንክና የመድን አገልግሎቶች በመስጠት በሩብ ዓመቱ ብር 45 ነጥብ 19 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅደው ብር 43 ነጥብ 68 ቢሊዮን ወይም የዕቅዳቸውን 97 በመቶ ማግኘት በመቻላቸው  ነው፡፡

ከተገኘው ከአጠቃላዩ  የብር 8 ነጥብ 48 ቢሊዮን ትርፍ ከፍተኛውን ብር 7 ነጥብ 38 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 77 በመቶ ያከናወነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡ ይኸው ባንክ ከአጠቃላዩ የዘርፉ ትርፍ 87.08 በመቶ ያህል ድርሻ ይዟል፡፡ 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብር 565 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 93 በመቶ በመፈጸም ከአጠቃላዩ የዘርፉ ትርፍ በሁለተኛ ደረጃ 6 ነጥብ 67 በመቶ ድርሻ አበርክቷል፡፡ አፈጻጸሙን አሻሽሎ በዚህ በጀት ዓመት ወደ ትርፋማነት የመጣው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ ብር 530 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 388 በመቶ ሊያተርፍ ችሏል፡፡ በዚህም ለዘርፉ አጠቃላይ ትርፍ የ6 ነጥብ 25 በመቶ አስተዋጽኦ በማድረግ ሶስተኛ  ደረጃን ይዟል፡፡

በግምገማዎቹ ማጠቃለያ ላይ የድርጅቶቹ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተጠቅሶ፣በሀብት አሰባሰብ፣በውጭ ምንዛሪ ግኝት እና ለዘርፉ አስፈላጊ በሆነ የሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክረው በበጀት ዓመቱ የተያዙ ግቦችን በከፍተኛ ውጤት ስኬታማ ለማድረግ የየድርጅቶቹ ቦርዶች፣የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች እያደረጉ ያሉትን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

በኤጀንሲው ስር ካሉና በኮሙኒኬሽን ዘርፍ ከተሰማሩ የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮ-ቴሌኮም በ2013 በጀት የመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት  በጊዚያዊ ሂሳብ መረጃ መሠረት ከታክስ በፊት ብር 14 ነጥብ 58 ቢሊዮን ወይም ከዕቅዱ 118 በመቶ ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገቡ ሰሞኑን መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

(ምንጭ፡- ወንድአፍራሽ አሰፋ – የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top