Connect with us

የሚሊኒየም አዳራሽ ቅሬታ!..

የሚሊኒየም አዳራሽ ቅሬታ!..
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የሚሊኒየም አዳራሽ ቅሬታ!..

የሚሊኒየም አዳራሽ ቅሬታ!..

(አስራት በጋሻው)

ይህ ጊዜ አልፎ ይላል፤ የሚሊኒየም አዳራሽ ቅሬታ ሲጀምር። ይህ ጊዜ አልፎ ለመወቃቀስ ያብቃን እንጂ እኔም እንዳንተው ነበርኩ ፡፡ ቴዲ አፍሮን፣ ሃጫሉን እና ሌሎችም አስጨፍሪያለሁ ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን፣ ኃይለማርያምን፣ ዶ/ር አብይንም፣ ኘረዝደንት ኢሳያስንም አስተናግጂያለሁ ፡፡

ስብሰባ እና ኤግዚቢሽን ሆቴል ሾው በዓመት አንዴ ሲደረግ ተመራጭ ነበርኩኝ ፡፡ ከፍ ያሉ ደረጃ የወጣላቸው ኮንፍረንሶችንና ፎረሞችን አካሂጃለሁ ፡፡ለቅሶ እና ሰርግንም አስተናግጃለሁ ፡፡ ሽልማትና የፓርቲ ተሃድሶን አይቼበታለሁ ! የሙዚቃ ድግሱ በኔ ያምር ነበር ። የኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችን አይቻለሁ፡፡

በመንገድ ብቻ ተለያይተን እንዲህ መሆኔ ይከፋኛል ፡፡አካፋይ መንገድ ተሻግሬ የልቤን አልነግርህ !

አንተ ገና በሰው አእምሮ ሳለህ እኔ ነበርኩ ፡፡አንተ ሆቴል ከመሆንህ በፊት  የምዕተ አመቱ ማብሰሪያ ነበርኩ፡፡  ለልደት ብቻ ሻማ እንደሚበራ የተነገረን ጊዜም  ነበርኩ ፡፡መለስ በሱዳንኛ ሙዚቃ ያስነኩት ከኔ ጋር ነው ፡፡

ለሁሉም ጊዜ አለው ፡፡ ያ ወቅት አለፈ ፡፡ ዛሬ ኮሮና ጉልበቱን የሚትፈሽበት ሆስፒታል ሆንኩልህ ፡፡ ያኔ ቪ8 ሲመላለስ እንዳልነበረ አምቡላንስ ጆሮዬን ያደነቁረኛል፡፡ ሀኪሞች ያለ የሌለ አቅማቸውን ተጠቅመው በሽተኛ  ለማዳን ይረባረባሉ ፡፡ ነጭ ገዋን የለበሱ ሀኪሞች ነፍስ ለማትረፍ ይዋከባሉ ፡፡

ያንተ ሰዎች ነጭ ለብሰው ምግብ ያበስላሉ ፡፡ ግዴለም ይሁን  ብዬ ለማለፍ አቅሜ አልፈቀደልኝም ፡፡መቼ ይሆን ያ ጊዜ የሚመለሰልኝ ? ወገን ኮሮና ለመኖሩም እየረሳ፣ የኔም ወደ ቀድሞ ስራ መመለስ ቀኑ እየረዘመ ተስፋ እያስቆረጠኝ ነው ፡፡ ማስክ ማድረግ እንዴት ያቅታል ? መራራቅስ ምን አስቸገረን ? ኮሮና አዲስ አበባ ገባ የተባለ ጊዜ የነበረው ጥድፊያ የት ገባ ?

ዛሬም ያንተ ሰዎች በክፉ ያዩኛል ፡፡ትኬት ቆርጠው ተሰልፈው እንዳልገቡ ይሸሹኛል  ፡፡ ቆመው ያየኻቸው ተኝተው ይመጣሉ ፡፡ ሰላምታ እየሰጡ የገቡ እንግዶቼ ፈገግታቸው ተሰርቆ አፋቸውን ተሸብቦ ይገባሉ ፡፡

በአምቡላንስ ገብተው በሬሳ መኪና ሲወጡ  ማየት ሰለቸኝ ፡፡ ከኮረና በሽታ አገግመው የሚወጡት ሳይ ነፍሴ ትመለሳለች ፡፡ ተስፋዬ ይለመልማል ፡፡ ሆኖም ሆኖም አይቆይም!!

አንተ ግን ዛሬም ታስጨፍራለህ ፡፡ትዝብት ብቻ እንዳይመስልህ ፡፡የኔ ወቀሳ ሊሰማህ የሚችልበት ቀን ሲደርስ ሁሉን ታገኘዋለህ ፡፡

አንተ ጋ አልጋ የያዙ ጸሀይ ስትወጣ ለቀው ይሄዳሉ ፡፡ነገር ግን የኔ ሰዎች ከምሽት እስከ ንጋት፣ ከቀን እስከ ሳምንት፣ ከሳምንት እስከ ሳምንት ከኔ ጋር ናቸው ፡፡

ያን ሰሞን ሲጫወት ጥርስ የማያስከድነው ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይመስለው የቡልቡላው ጎረቤታችን ባዪ ከዘመናዊው የግል ሆስፒታል ወደ እኛ ተዛውሮ ሃያ አራት ሰዓት ሳይሞለው ሞተ ፡ ፡ አየር አየር እንዳለ፣ ልጄ ልጄን እንዳለ ተነጠቀ ፡፡

አንተ ምን አለብህ?!.. አሁንም ፈገግ ብለው የሚገቡ ደንበኞችህ ቢቢዛ ጠግበው አፋቸውን እየጠረጉ ይወጡ ይሆናል ፡፡

ሰርግና ስብሰባውን ተያይዘሀል ፡፡ ምን ይደረግ !!

አንተ እንዳልከው እድሌ መክኖ ነው ! አንተም እድልህ ሰምሮ ነው ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top