Connect with us

አዲስ የሚወጡ ምርጥ የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልም እና ዘጋቢዎች

አዲስ የሚወጡ ምርጥ የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልም እና ዘጋቢዎች
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጅና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

አዲስ የሚወጡ ምርጥ የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልም እና ዘጋቢዎች

አዲስ የሚወጡ ምርጥ የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልም እና ዘጋቢዎች

ለወትሮው ስሜትን እየጋለቡ ወደማናውቀው ምዕናባዊ አለም የሚወስዱ ፊልሞችን ለተመልካቾች በማድረስ የሚታወቀው ሆሊዉድ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተከትሎ ያሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት 2020 በመሰናክሎች የተሞላ አድርጎበታል፤ በርካታ ፊልሞችም የመለቀቂያ ቀናቸው እንዲዘዋወር ጭምር ሆነዋል፡፡ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ግን እነዚህ የመለቀቂያ ቀናቸው የተላለፉ ፊልሞችን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ የሳይንሳዊ ልብወለድ እንዲሁም ሳይንስ ተኮር ዘጋቢ ፊልሞች ለተመልካች ይደርሳሉ፡፡

ኤ ኳየት ፕሌስ ክፍል ሁለት፤ ያለንበት የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ተከትሎ ለሁለት ጊዜያት ያህል የሚለቀቅበት ቀን የተራዘመ ቢሆንም ይህ በኤምሊ ብላንት መሪ ተዋናይነት እና በባለቤቷ ጆን ክራሲንስኪ ተፅፎ ዳይሬክት የተደረገው አስፈሪ ፊልም በመጪው ሚያዝያ ለዕይታ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ ድምፅን ሰምተው በሚያድኑ አውሬዎች በተሞላው የድህረ ውድመት አካባቢ መኖርያውን ያደረገው የአበት ቤተሰብ ስፍራው ላይ በተጨማሪነት ሌሎች አደጋዎች ሲገጥማቸው ፊልሙ ያሳያል፡፡

ባዮስ፤ ሌላኛው የሚታይበት ጊዜ ከ2020 የተላለፈ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም ሲሆን በመሪ ተዋናይነት የሚደምቀው ቶም ሄንክስ በአንድ ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ አማካኝነት ዶጋ አመድ በሆነ የሰሜን ማዕከላዊ የአሜሪካን ክፍል ውስጥ እርሱ ሲሞት ውሻውን ይንከባከብለት ዘንድ ሮቦት የሰራ ግለሰብ ሆኖ ይተውንበታል፡፡

ቶፕ ገን ማቭሪክ፤ በምዕናቡ ዓለም ውስጥ ጠልቀው ከሚገቡ የሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልሞች በተጨማሪም በአውሮፓውያኑ 1986 ተሰርቶ የነበረው “ቶፕ ገን” ፊልም ቅጣይ የሆነው ቶፕ ገን፤ ማቭሪክ ከወራት በኋላ ለስክሪን የሚበቃ ይሆናል፡፡ መሪ ተዋናዩ ቶም ክሩዝ የፊዚክስ ህጎችን የሚገዳደርበት ፊልሙ መጪው ሐምሌ ላይ ይሆናል ለተመልካች ዕይታ የሚቀርበው፡፡

ዶንት ሉክ አፕ፤ ፊልሙ ዝነኞቹ ተዋናዮች ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ እና ጄንፈር ላውረንስ ወደ ምድር አቅጣጫ እየገሰገሰ ያለ አንድ አጥፊ ሜትሮይትን አስመልክተው ሰዎችን ለማስጠንቀቅ የሚባዝኑ ሁለት የህዋ ተመራማሪዎችን ገፀ ባህርይ ተከላብሰው ይተውኑበታል፡፡ አሁን ላይ በቦስተን ቀረፃው እየተከናወነለት ያለው ዶንት ሉክ አፕ ከሁለቱ በተጨማሪም ሌሎች የሆሊውድ ዘነኛ ተዋንያንን ይዟል፡፡

ባቢሎን፤ የላላ ላንድ ፊልም ዳይሬክተሩ ዳሚየን ሻዜል ፊልም የሆነው ባቢሎን ከድምፅ አልባዎቹ ዘመን አንስቶ እስከ ባለ ድምፆቹ ድረስ እንዴት በጊዜ ሂደት ውስጥ የፊልም ቴክኖሎጂዎች እንደተለወጡ የሚቃኝ ይሆናል፡፡

ከነዚህ የሲኒማ ፊልሞች በተጨማሪ የተለያዩ ሳይንስና የሳይንስ ስብዕናዎች ላይ ያተኮሩ ዘጋቢ ፊልሞችም በዓመቱ ለህዝብ የደረሱና የሚደርሱ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ዘጋቢዎች አንዱ በአየር ንብረት ጠበቃነቷ የምትታወቀው ታዳጊዋ ግሪታ ተንበርግ ላይ የሚያተኩረው “አይ አም ግሪታ” የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም ይገኝበታል፡፡ 

በተጨማሪም ስለ ስመጥሩ የፊዚክስ ተመራማሪ ስቴፈን ሀውኪንግ ከዚህ በፊት ያልታዩ ጉዳዮችን የሚዳስሰው “ሀውኪንክ” የተሰኘው የስካይ ዘጋቢ ፊልመ ተጠቃሽ ነው ሲል ኒው ሳይንቲስት በምንጭነት ጠቅሶ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጅና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዘግቧል።

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top