Connect with us

ለማንም ተብሎ አንገት አይደፋም

ለማንም ተብሎ አንገት አይደፋም
Photo Credited Late PM Aklilu Habtewold's Family

ባህልና ታሪክ

ለማንም ተብሎ አንገት አይደፋም

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከተማ ይፍሩ ልጅ መኮንን ከተማ ይፍሩ ስለጸሐፌ ትዕዛዝ ይህንን ብሏል።

ለማንም ተብሎ አንገት አይደፋም

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሥራያቤታቸውን የለቀቁ ሰሞን በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ እንዲህ ብለው ነበር… “ኢትዮጵያ አገራችን ካሏት በአገር ፍቅር ስሜት ከታነፁ አንጋፋ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነውና እነ አክሊሉ ሃብተወልድና ከተማ ይፍሩ የመሳሰሉ አገር ወዳዶችና ስመ ጥር መሪዎችን ባፈራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመድቤ አገሬን በፍቅር በማገልገሌ ሁልጊዜም ኩራት ይሰማኛል።” እሳቸው አክሊሉ ሃብተወልድን አገር ወዳድ ብለው ሲገልፀዋቸው እዛው ብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ያሉት ደግሞ ሌላ ይሏቸዋል። ለምን ይሆን?

ትልቅ ሥራ አበርክተው የሄዱትን የኢትዮጵያ መሪዎች ከሆነ ብሔር ናቸው ብለው ጥቂቶች ስለሚያምኑ ሊያሳንሷቸው ሲሞክሩ አያለሁ። ይሄ ድርጊት ስርም እየሰደደ ነው። ለምን እንደሚደረግም ግልፅ ነው። አንድን ብሔር ታሪክ አልባ አርጎ አንገት ለማስደፋት ሆን ተብሎ የተፀነሰ ሴራ ነው። አይ አለማወቅ። ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከሀገርም አልፈው በአለም ደረጃም በሥራቸው የታወቁ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር እንደነበሩ ስለማያውቁ ነው። እሳቸው እኮ አንዱን ከሌላው የማያበልጡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።

ኢትዮጵያ እንደማንኛውም አገር ታሪክ አላት። ታሪክ ተሰርቶ የተቀመጠ የቆየ ስራ ነው። ማየት እንጂ መቀየር የማንችለው። ሲያሻን ለእኛ ጥቅም ብለን ወደኅላ ሄደን ምናስተካክለው አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የማይሞከር ነገር ስለሌለ ወደ ኅላ ሄደን የተሠራውን ሁሉ እኛ በምንፈልገው መልክ ለማስቀመጥ ሙከራ እያደርግን ነው። ወደፊት እንደመሄድ ወደ ኅላን ምን አመጣው?

ጥላቻ ከሁሉም በላይ እራስን ነው የሚጎዳው። ለሀገር የመሥራት አጋጣሚ ስታገኙ እባካችሁ ተጠቀሙበት። እናንተም ወደፊት ስማችሁ በጥሩ ሊነሳ ይችላል። ባሉበት ጊዜ ከተቻለ የበለጠ ሠርቶ ማለፍ ነው እንጂ ያለፉትን ታላላቅ የኢትዮጵያን ልጆች መንካት የራስን ጉድለት በአደባባይ ማሳየት መሆኑን ማን በነገራችሁ። እኔም ሆነ ሌላው የሚታየን ይሄው ነው።

እስቲ እንደ ምታሟቸው አባቶቻችን እስከ ዛሬ ድረስ ወደር የሌላቸውን እንደ እነ ኢትዮጵያ አየር መንገድን; አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ; የአፍሪካ ህብረት; ወዘተ የመሳሰሉትን ለመሥራትና እነሱ እንዳደርጉት እናንተም ለሚቀጥለው ትውልድ ለማበርከት ሞክሩ። እንደ አባቶቻችን አያቶቻችን እና ቅድመ አያቶቻችን በሥራ እንጂ በንግግር ግዚያችሁን አትጨርሱት። የኢትዮጵያ ህዝብ ከናንተ የሚጠብቀው የጎደለውን እንድታሟሉለት እንጂ ወደኅላ ሄዳችሁ ታሪክን እንድትቀይሩለት አይደለም።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top