Connect with us

ሀብት ያላስመዘገቡ በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ተጠያቂ ሊደረጉ ነው

ሀብት ያላስመዘገቡ በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ተጠያቂ ሊደረጉ ነው
የኮምሽኑ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ዜና

ሀብት ያላስመዘገቡ በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ተጠያቂ ሊደረጉ ነው

ሀብት ያላስመዘገቡ በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ተጠያቂ ሊደረጉ ነው

 197 የሚሆኑ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች፣ በፌደራል መንግሥት ሥር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጀች፣ የአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች፣ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መሠረት የሠራተኞቻቸውን ሀብት ሙሉ በሙሉ አስመዝግበው አለማጠናቀቃቸውን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በዚህ መሠረት 109 የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የፌደራል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ በፌደራል መንግሥት ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፣ 60 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት፣ ክፍለ ከተማና ወረዳዎች እንዲሁም 28 የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተቋማትና ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የሠራተኞቻቸውን ሀብትና ንብረት ሙሉ በሙሉ ያላጠናቀቁ ናቸው፡፡

ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው አያወቁ በቸልተኛነትና ፍቃደኛ ባለመሆን ሀብታቸውን ባሰመዘገቡ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎችና ሠራተኞች ላይ በሕጉ መሠረት ከጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለመንም ቅድመ-ሁኔታ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚሽኑ በአፅዕኖት ይገልፃል፡፡

በተያያ ዜና 311 የሚሆኑ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች፣ የአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች፣ በፌደራል መንግሥት ሥር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጀች በተቋማቸው የሚገኙ ሠራተኞቻቸውንና አመራሮቻቸውን ሀብትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲመዘገብ ማድረግ ችለዋል፡፡

በዚህ መሠረት 149 የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የፌደራል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ በፌደራል መንግሥት ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፣ 142 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት፣ ክፍለ ከተማና ወረዳዎች እንዲሁም 21 የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተቋማትና ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የሠራተኞቻቸውን ሀብት አስመዝግበዋል፡፡

ተቋማቱ በመንግሥት ተሿሚዎችና በመንግሥት ሠራተኞች ላይ የሀብትና ንብረት ምዝገባ ያደረጉት የሀብትና ንብረት ማስመዝገብ ግዴታ በሚጥለው የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት ነው፡፡

ይህን ድንጋጌ ተግባራዊ ለማድረግ የፊደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመላው ሀገሪቱ የሀብትና ንብረት ምዝገባ ሥራን ተግባራዊ ለማድረግ በተለይ በዚህ በጀት ዓመት  ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ 

የኮሚሽኑን ጥረት በመደገፍ ሀላፊነታቸውን ለተወጡ የየተቋማቱ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎችና ይህን ሥራ በበላይነት በማስተባበር ገንቢ ሚና ለተጫወቱ የየተቋማቱ አመራሮች ሀላፊነታቸውንና ግዴታቸውን በሕጉ መሠረት ስለተወጡ ኮሚሸኑ የላቀ ምስጋና ያቀርብላቸዋል፡፡

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት የሥራ ሀላፊዎችንና የሠራተኞችን የሀብት ምዝገባ ሥራ ያላጠናቀቁ ተቋማትን ዝርዝር በአጭር ጊዜ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆ ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎችንና ሠራተኞችን በሕጉ መሠረት ከጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ይገልፃል፡፡

(የኮምሽኑ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top