Connect with us

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ (ድል ቁርሱ) በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ክህደትና ግፍ  ይናገራሉ

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ (ድል ቁርሱ) በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ክህደትና ግፍ ይናገራሉ
Ethiopian News Agency

ዜና

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ (ድል ቁርሱ) በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ክህደትና ግፍ  ይናገራሉ

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ (ድል ቁርሱ) በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ክህደትና ግፍ  ይናገራሉ

ጁንታው “ሠሜን ዕዝን የፌዴራሉ መንግሥት አሐዳዊ ሆኗል ብዬ አሣምኜ ከእኔ ጋር አሠልፈዋለሁ” ብሎ ነበር ያቀደው፤

ሌላው ልዩ ኃይል አዘጋጅቷል፤ ሚሊሻ በብርጌዶች አዘጋጅቷል፤ በየመንደሩ ያለውን ሚሊሻና ተራ ፖሊስ ስናስበው እንኳን እስከ መቶ ሺህ ለውጊያ የተዘጋጀ ኃይል ነበረው፤

ወደ ሠላሳ ሺህ የሚደርስ የሠሜን ዕዝ ሠራዊት ደግሞ ከእኔ ጋር ማሰለፍ እችላላሁ ብሎ አስቧል፤ ይኼን ለማሣካት ደግሞ በትግርኛ ተናጋሪዎች በኩል ውስጥ ለውስጥ ሠርቷል፤

ይኼን ይዞ ሊያደርግ ያሰበው በጎንደር አንድ ግንባር፣ በራያና አፋር ሌላ ግንባር አድርጎ ጠቅላላ ሥርዓቱን በሀይል የመቀየር የጥፋት ዕቅድ ነበረው፤

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ያፈርሣል፤ ከዚያ ወደ ሥልጣን ይመጣል፤ ሽግግር መንግሥት ያውጃል፤ መጀመሪያ ቃል የገቡለትንና ቃል የገባላቸውን ኃይሎች አሰባስቦ የሽግግር መንግሥት ይመሠርታል፤ ይኼ ነበር ዕቅዱ፤

ይኼ ሲሆን ሕዝቡ ዝም ይላል ወይ? ካልከኝ፤ ዝም አይልም። ከነበረው ጭቆና ወጥቻለሁ እያለ፣ የባሰ የሚጨቁን ኃይል እየመጣበት ስለሆነ እንኳን መጣ ብሎ ቄጠማ ጎዝጉዞ እንደ 1983 ዓ.ም አይቀበለውም ነበር፤

ሁሉም ራሱን ለመከላከል ርምጃ ይወስዳል፤ ስለማይቀበለው ሀገሪቷ ትፈርሣለች፤

ሰሜን ዕዝ ሕገ መንግሥታዊ ሠራዊት ስለሆነ ይኼን አንቀበልም ብሏል፤

አንቀበልም ሲል እያንዳንዱ በያለበት እንዲወረር፣ እንዲከበብ ነው ያደረጉት፤

በግድ አንበርክከው እሽ ያላቸውን አሰልፈው፣ እንቢ ያላቸውን ገለው፣ ትጥቁን ወርሰው፣ ወደ ዋናው ዕቅዳቸው ሊቀጥሉ ነበር፤

ሠራዊቱ ግን እንቢ አላቸው፤ ተዋጋ፤ ተከቦ ውሃ፣ ምግብ እንዳያገኝ አድርገው፤ ተስፋ ቆርጦ እጅ እንዲሰጥ ለማድረግ ሞክረዋል፤

በጣም ኃይለኛ የሆነባቸውን ደግሞ ገደሉ፤ ትናንሽ ዩኒቶችን መርጠው በመክበብ ተታኩሰው፣ ዩኒቱ ጥይት ሲጨርስ እየያዙ ልብስ እያስወለቁ እጅ ወደ ላይ እያደረጉ ረሸኑ፤

አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መለዮ የለበሱ ደብተርና መጻፊያ የያዙ፣ ጠበንጃ ያልያዙ ወታደሮችን ይዘው ማርከናል ብለው ጨፈሩ፤

ሠሜን ዕዝ በያለበት ካምፕ የከበበውን የጁንታ ኃይል ደምስሶ፤ እንደማይቻል አሣይቶ ከዚያ በኋላ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት፣ ከከበባው ትጥቁን ይዞ ሰብሮ ወጥቷል፤ የቀረው ትጥቅ መንቀሳቀስ የማይችል ነው፤

ሠራዊቱ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጀግንነት ተከስቷል፤ እልህ፣ ቁጭት ተፈጠረ፤

ሠራዊቱ እንዴት እንደዚህ ያደርጉናል ብሎ ‹እናቴ፣ አባቴ፣ ወዳጄ፣ ወንድሜ እያለ አብሮ የበላ፣ የጠጣ፣ የተጋባ ትምህርት ቤት የሠራላቸውን፤ መንገድ የሠራላቸውን፤ እህል እያጨደላቸው፤ ሁሉን ሲያደርግላቸው ሃያ ዓመት የከረመ ልጃቸውን እንዴት ይበላሉ?› ብሎ ሠራዊቱ በጣም ነው የተቆጣው፤

በራሱ በጁንታው ውስጥም መፍረክረክ ፈጥሯል፤  ምክንያቱም በውስጣቸው ያልጠበቁት ሰዎችም አሉ፤

“የተባባልነው እኮ! ሠሜን ዕዝን አሣምነን ከእኛ ጋር ተሰልፎ ወደ መሃል ሀገር እንገባለን ነው እንጂ፤ ሠራዊቱን እንወራለን፣ እንመታለን አልተባባልንም” በሚል መፍረክረክ በውስጡ ፈጥሯል፤

የትግራይ ሕዝብም ‹ያላችሁት እኮ ሠራዊቱን አሰልፈን ወደ መሃል ሀገር እንሄዳለን ነው እንጂ፣ ሠራዊቱን እንደምትወጉ አናውቅም። የሠራችሁት ትክክል አይደለም፤ ከእናንተ ጋር አንቆምም› ብሏል፤

የኢትዮጵያ ሕዝብም ቀፎው እንደተነካበት ንብ ነው ‹ሆ› ብሎ የጁንታውን ተግባር የተቃወመው። የሠራዊቱም የሞራል ምንጭ ሆኗል፤

ሌላው ቀርቶ ከጫፍ እስከ ጫፍ አስታጥቀውት እንዲዋጋ ሲጋብዙት የነበረው የትግራይ ሕዝብ “እኛ እንዴት ሠራዊት እንወጋለን” ብሎ ትጥቁን እያስረከበ ከሠራዊቱ ጎን ነው የቆመው፤

ጁንታው ብቻውን ነው የቀረው፤ ከዚያ በኋላ ያለው ነገር የወታደራዊ ጥበብ ጉዳይ ነው፤

ወታደራዊ ጥበቡ ደግሞ ተሠርቷል፤ ውጊያውም በሁለት ሣምንታት አልቋል፤

የአንድ ሣምንት የጉዞ ጊዜ ብትጨምርበት በሦስት ሣምንታ አልቋል፤

ከፎክላንድ ደሴት እና ከስድስቱ ቀን ጦርነት ሌላ በእንዲህ ዓይነት አጭር ጊዜ ጦርነት ያለቀበትን ጊዜ እኔ አላውቅም፤

ኢ ፕ ድ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top