Connect with us

ኢትዮጵያን ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያገናኘው መንገድ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያን ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያገናኘው መንገድ ሊገነባ ነው
ኢትዮ መንገዶች ባለስልጣን

ዜና

ኢትዮጵያን ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያገናኘው መንገድ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያን ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያገናኘው መንገድ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያን ከኤርትራ የአሰብ ወደብ ጋር የሚያስተሳስረው  የሜሎዶኒ መገንጠያ – ማንዳ – ቡሬ  የመንግድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊገነባ ነው።

በነገው ዕለትም ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፕሮጀክቱን በይፋ የማስጀመር መርሃ ግብር ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዕለቱ በሚኖረው መርሃ -ግብርም ግንባታው የተጠናቀቀው የዲቾቶ – ጋላፊ መገንጠያ – ኤሊዳር – በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም ይመረቃል።

የሜሎዶኒ መገንጠያ – ማንዳ – ቡሬ  መንገድ ሲጠናቀቅ   ወደ አሰብ ወደብ የሚዘልቅ መንገድ እንደመሆኑ ለኢትዮጵያ የተሻለ የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ መሳለጥ አይነተኛ ሚናውን ይጫወታል፡፡

71 ነጥብ 65 ኪ. ሜ የሚረዝመውን ይህን ፕሮጀክት በብር 2 ቢልየን 085 ሚልየን 985 ሺህ 162 ብር ከ6 ሳንቲም በሆነ ወጪ ጨረታውን አሸንፎ ግንባታውን የሚያከናውነው ሻንዶንግ ሊኪኖ ግሩፕ የተባለ የወጭ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው። 

የግንባታውን የማማከርና የቁጥጥር ስራ ደግሞ ስሜክ ኢንተርናሽናል እንዲሁም ቫሊዩ ኢንጅነሪንግ በንዑስ ተቋራጭነት ይሳተፋል ።

ለፕሮጀክቱ ግንባታ ማስፈጸሚያ   ወጪም የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡

በአገልግሎት ሳቢያ የተጎዳ የአስፋልት መንገድና ከ6 ሜትር ያልበለጠ  ስፋት የነበረውን በቀጣይ ከተሞች ላይ  19 ሜትር እንዲሁም በገጠር ደግሞ የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 1ዐ ሜትር የጎን ስፋት  እንዲኖረው ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል። 

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለአመታት ተቋርጦ የነበረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ዳግም በመጀመሩ መስመሩን ለሚጠቀሙ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በተያያዘ ዜናም  78 ኪ.ሜ የሚረዝመው  የዲቾቶ – ጋላፊ መገንጠያ – ኤሊዳር – በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን ፕሮጀክት በነገው ዕለትም በይፋ ይመረቃል።

መንገዱን ለመገንባት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታ ያካሄደው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተባለ የመንግስት ልማት ድርጅት ነው።

የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድርና ከሲም አማካሪ መሃንዲስ በጥምረት ተሳትፈውበታል፡፡ 

የኢትዮጵያ መንግስትም የመንገድ ግንባታውን ለማካሄድ የዋለውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሸፍኖታል፡፡ 

አካባቢው ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ግንባታው በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ሲሆን   ይህም የአየር ጸባዩን የመቋቋም እና የግልጋሎት ዘመኑ እንዲጨምር ያደርጋል ።

የዲቾቶ – ጋላፊ መገንጠያ – ኤሊዳር – በልሆ መንገድ መገንባት አዲሱን የታጁራ ወደብ በአማራጭነት  ለመጠቀም የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር በነባሩ ጅቡቲ ወደብ ይፈጠር የነበረውን የትራንስፖርት ጫና እና መጨናነቅ እንደሚያቃልለው ይጠበቃል።

ፕሮጀክቱ የአገሪቷ የወጪ ገቢ ንግድ የሚካሄድበት ኮሪደር እንደመሆኑ መስመሩን የሚጠቀሙ ብዙ ቁጥር ያላቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች ክብደት የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ታሳቢ ያደረገ ነው ፡፡ (ኢትዮ መንገዶች ባለስልጣን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top