Connect with us

አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ አንዳንድ የይዘት ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጠየቁ።

በመተከል ጥቃት ጉዳይ ፓርላማው ቁርጥ ውሳኔ አሳለፈ
ሕ/ተ/ም/ቤት

ዜና

አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ አንዳንድ የይዘት ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጠየቁ።

አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ አንዳንድ የይዘት ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጠየቁ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ አስረጂዎች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ የተሳተፉት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በረቂቁ በተጠቀሱ አንዳንድ ይዘቶች ላይ መሻሻሎች ሊደረግባቸው ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ተወካይ አቶ አማረ አረጋዊ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በስራ ላይ ከነበረው የተሻለ መሆኑን ገልፀዋል።

ይሁንና በረቂቁ በሚቋቋመው የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ ተቋም የሚሰየሙት የቦርድ አባላት ለጋዜጠኞች ደንብ ያወጣሉ የሚለው መቀየር አለበት ብለዋል።

መገናኛ ብዙሃን እርስ በእርሳቸው መገማገም የሚያስችሏቸውን የሥነ-ምግባር መመሪያዎች ራሳቸው በምክር ቤት በኩል ሊያወጡ ይገባል ነው ያሉት።

ጋዜጠኛ ታምራት ሃይሉም በተመሳሳይ ከጋዜጠኞች ምክር ቤት /ካውንስል/ ውጭ ሌላ አካል የሥነ-ምግባር መመሪያዎችና ደንብ ማውጣት የለበትም ሲል አስተያየት ሰጥቷል።

በሌላ በኩል በረቂቁ የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚዎች ከሚዲያ ባለቤትነት መከልከል እንዳለባቸው በግልፅ መጠቀስ እንዳለበት ተናግሯል።

ረቂቁ የግልና የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን እኩል ሊወዳደሩበት የሚችሉበትን ማዕቀፍ ሊያመላክት እንደሚገባም ጠቁሟል።

ስም ማጥፋት በወንጀል መዳኘት የለበትም የሚለው ከሚዲያ ውጭ በሌሎችም አውዶች ተግባራዊ መሆን አለበት በማለትም ሃሳብ ሰጥቷል።

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተወካይ አቶ ማናዬ ዓለሙ በበኩላቸው በረቂቁ የሚቋቋመው የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ ተቋም ገለልተኛ መሆን አለበት ብለዋል።

ያም ሆኖ ለተቋሙ የሚሰየመው ዋና ሃላፊ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ ገለልተኝነቱ ላይ ጥያቄ አያስነሳም ወይ ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋሙን ሃላፊ መሾማቸው የገለልተኝነት ጥያቄ አያስነሳም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ረቂቁ ከዚህ ቀደም የነበረውን የዴሞክራሲ ተቋማት አሰራር የተከተለ መሆኑን ጠቅሰው የቦርዱን አባላት የጥቅም ግጭት በሚመለከት በረቂቁ በግልጽ ተቀምጧል ብለዋል።

ያም ሆኖ የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚዎች በተለይም የፖለቲካ ተፅዕኖ እንዳያሳድሩና ተፅዕኗቸውንም መቀነስ በሚያስችል መልኩ ረቂቁ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ስም ማጥፋት ከሚዲያ ውጭ በሌሎችም አኳኋኖች በወንጀል መጠየቅ የለበትም የሚለው ጥያቄ ረቂቅ አዋጁ ሚዲያን ብቻ ስለሚመለከት ለሚዲያ ሥራ ብቻ ይውላል ብለዋል።

በሌላ በኩል የቦርዱ አባላት የሥነ-ምግባር መመሪያዎች እንዲያወጡ የተደረገው ዓለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተዘጋጀ እንጂ ነጻነቱን ለመጋፋት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ያም ሆኖ የሚያወጡት ዝቅተኞቹን የመመሪያ ደረጃዎች መሆኑን ነው ያብራሩት።

በሌላ በኩል ረቂቁ ለመንግሥትና ለግል የመገናኛ ብዙሃን እኩል ምህዳር የሚፈጥርና ሁሉቱም በየፊናቸው ሥራቸውን በእኩልነት መሥራትj እንደሚያስችላቸው ጠቅሰዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ከባለሙያዎቹና ከባለድርሻ አካላት የተሰነዘሩ አስተያየቶችን በግብዓትነት በመውሰድ አስረጂዎች አስተካክለው ዳግም እንዲያቀርቡ አሳስቧል።(የሕ/ተ/ም/ቤት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top