Connect with us

የዛሬዎቹስ ከሕወሓት ‘የውድቀት ታሪክ’ ይማሩ ይሆን?!

የዛሬዎቹስ ከሕወሓት ‘የውድቀት ታሪክ’ ይማሩ ይሆን?!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የዛሬዎቹስ ከሕወሓት ‘የውድቀት ታሪክ’ ይማሩ ይሆን?!

የዛሬዎቹስ ከሕወሓት ‘የውድቀት ታሪክ’ ይማሩ ይሆን?!

በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

‘‘የታሪክ ዓላማው ሕዝብ ያለፈውን ዘመን ከፍታና ዝቅታ አስታውሶ፣ የአሁኑ ትውልድ ካለፈው ትውልድ በጎ ጎኖች ትምህርት ወስዶ፣ ከችግሮቹ ተምሮ በኑሮው መሻሻል እንዲያሳይ ማድረግ ነው፡፡’’ (ነፍሰ ኄር ፕ/ር ጋሼ መስፍን ወ/ማርያም)

በሐር ጥቅል፣ በወርቅ እንክብል ሲቀማጠሉ የነበሩ፤ ዘንግ በተወረወረ፣ ወፍ በበረረ ቁጥር ‘ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት’ ሲያስብሉ የኖሩ፤ ከፊት ከኋላቸው እልፍ አእላፍ ሠራዊትን ያስከተቱ፣ ከአደባባይ ጀምሮ ጓዳና እልፍኛቸው ድረስ ቋሚ ለጓሚ፣ አሸከር ደንገጡር ያሰልፉ የነበሩ- የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት ባለሥልጣናት እንደዛ ተጎሳቁለውና ተዋርደው፣ በእጃቸው ላይ ሠንሠለት ተጠልቆላቸው ሳያቸው፤ በንስሓ ዘመናቸው ‘ጦር ክተት’ ብለው ወደ በረሃ የወረዱ አረጋውያኑ የሕወሓት ሰዎች አሟሟት ስመለከት፤ ያ ሁሉ ትዕቢትና ፉከራ ፍፃሜው ይህ መሆኑን ባሰብኩ ጊዜ- እነዚህ ወገኖች ከታሪክ ባለመማራቸውና የውድቀት ታሪክን ለመድገም የተፈረደባቸው መሆናቸውን አሰብኩና አዘንኩ፡፡

ይባስ ብሎም እነዚህ ሰዎች በክፉ ስብከታቸውና በሸንጋይ አንደበታቸው የክፋታቸው፣ የዓመፃቸው ተባባሪ ያደርጓቸውን የልጆቻቸውን የወገኖቻቸውን ሞትና መቃብር አይተው፣ እርማቸውን ለማውጣትም ሆነ እንደ ሀገር ወግ አልቀሰው ለመቀብር አለመታደላቸውን ባሰብኩኝ ጊዜ- ይህ የውድቀት ታሪክ አዙሪት፣ የደርግ መንግሥት ከዘውዱ ሥርዓት፣ የትናንትናው ሕወሓትም ከደርግ የውድቀትና የውርደት ታሪክ ለመማር አለመቻላቸውን አስረግጦልን አልፏል፡፡ 

የታሪክ ዓላማው ይላሉ ነፍሰ ኄር ፕ/ር ጋሼ መስፍን ወ/ማርያም፤ ‘‘የታሪክ ዓላማው ሕዝብ ያለፈውን ዘመን ከፍታና ዝቅታ አስታውሶ፣ የአሁኑ ትውልድ ካለፈው ትውልድ በጎ ጎኖች ትምህርት ወስዶ፣ ከችግሮቹ ተምሮ በኑሮው መሻሻል እንዲያሳይ

ማድረግ ነው፡፡’’ ግና ይህ እውነታ ዛሬም እንኳን በእኛ ዘመን ሰሚም ተርጓሚም ያገኘ አይመስልም፡፡

እናም የቀደሙት ካለፉበት የትናንትናው የውድቀትና የውርደት ታሪክ ለመማር ያልፈቀዱ ሁሉ የጥፋት ታሪክን እየደገሙ፣ ራሳቸውን ፍትሑ ለማይዛነፈው፣ ፍርዱ ለማይጓደለው የአምላክ ቁጣ ራሳቸውን ያዘጋጃሉ፡፡ በትናትናዎቹ የሕወሓት ባለሥልጣናትና ሽማግሌዎች ዘንድም የኾነው ይኸው እውነት ነው፡፡

‘‘እግዚአብሔር ሲቆጣ በትርን አይቆርጥም፣ ያደርገዋል እንጂ ለወሬ እንዳይጥም፡፡’’

እንዲሉ አበው ወእመው፤ እናም የእነዚህ ሰዎች ፍፃሜ ይህን የእግዚአብሔርን ዘላለማዊና ሕያው ቃል አስታወሰኝ፡፡

‘‘ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፤ ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት አዋርዳለሁ፡፡ ክፉዎችና ዓመፀኞች፣ ታላላቆችና ታናናሾች በምድራቸው ላይ ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፣ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም ስለ እነርሱም ገላን አይነጩላቸውም፣ ራስንም አይላጩላቸውም፤ ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፣ ስለ ልጆቻቸው፣ ስለ አባታቸውና እናታቸውም ሞት የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም፤ የኃጢአተኞች፣ የክፉዎች መብራት በድንገት ይጠፋል፤ ብርሃን በድንኳናቸው ውስጥ ይጨልማል መብራቱም በላያቸው ይጠፋል፤ የኃይላቸው እርምጃም ትጠብባለች፣ ምክራቸውም ይጥላቸዋል፡፡ 

እግራቸው በወጥመድ ትያዛለች፣ አሽክላ ሰኰናቸውን ይይዛል፣ በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመድ፣ በመንገዳቸውም ላይ ወጥመድ ለእነርሱ ተሰውራለች፡፡ ድንጋጤና ፍርሃት በዙሪያቸው ታስፈራቸዋለች፣ በስተኋላውቸም ሆና ታባርራቸዋለች፡፡ 

ኃይላቸውም በራብ ትደክማለች፣ መቅሠፍትም እስኪሰናከሉ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ የሰውነታቸው ብልቶች

ይጠፋሉ፤ የሞትም በኵር ልጅ ብልቶቻቸውን ይበላል፡፡ ከሚታመኑበት ድንኳን ይነቀላሉ፡፡ በድንኳናቸው/በቤቶቻቸው ውስጥ ለእነርሱ የማይሆነው ይኖራል፤ በመኖሪያቸውም ላይ ዲን ይበተናል፡፡ ሥራቸው ከበታቹ ይደርቃል፣ ጫፉም ከበላይ ይረግፋል፤ መታሰቢያቸው ከምድር ላይ ይጠፋል፣ ስምም አይቀርላቸውም፡፡

በእውነት የክፉዎችና የዓመፀኞች ሰዎች ፍፃሜያቸው ይህ ነውና፡፡’’ ‘‘በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም

ከፍ አድርጎአል፤ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል፡፡’’

(ቅድስት ድንግል ማርያም)

(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕ. ፲፮፣ መጽሐፈ ኢዮብ ምዕ. ፲፭ እና ምዕ. ፲፰፣ ሉቃ. ምዕ. ፩)

ሰላም!!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top