Connect with us

በአዳዲስ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራዎች እየተፋጠኑ ነው

በአዳዲስ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራዎች እየተፋጠኑ ነው
አ/አ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

ዜና

በአዳዲስ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራዎች እየተፋጠኑ ነው

በአዳዲስ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራዎች እየተፋጠኑ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቅርቡ ያስጀመራቸው የጋራ መኖሪያ ቤት የመንገድ ግንባታ ስራዎች በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛሉ፡፡

በያዝነው በጀት ዓመት ህዳር ወር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የግንባታ ስራቸው በይፋ ከተጀመሩት የመንገድ ግንባታ ኘሮጀክቶች መካከል ኮዬ ፈቼ  ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 2፣ ኮዬ ፈቼ  ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሎት 1፣ ኮዬ ፈቼ  ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 18 በአቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ናቸው፡፡

እነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የአስፋልትና የኮብል መንገዶች ሲሆኑ የአስፋልት መንገዶቹ አጠቃላይ 15.8 ኪ.ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ የጐን ስፋታቸው በአማካይ 12/40 ሲሆን  የኮብል መንገዶቹ አጠቃላይ 28 ኪ.ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 10/40 ስፋት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ የመንገድ ግንባታቸውን ለማከናወን 1,885,014,176.98 በጀት ተመድቦላቸዋል፡፡

የመጀመሪያው ኮዬ ፈቼ ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 11 የመንገድ ግንባታ ስራውን ሜልኮን ኮንስትራክሽን የሚያከናውነው ሲሆን የማማከር ስራውን ኘሮሚነንት ኢንጂነሪንግ ሶሉሽንስ እያከናወነው ይገኛል፡፡ የመንገድ ግንባታው 4 የአስፋልትና 15 የኮብል መንገዶች ሲኖሩት የአስፋልት መንገዶቹ 4.6 ኪ.ሜትር ርዝመትና  የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 12/40 ሜትር የጐን ስፋት ይኖራቸዋል፡፡ የኮብል መንገዶቹ 9.5 ኪ.ሜትር ዝርመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 10/20 ሜትር የጐን ስፋት አላቸው፡፡

ለመንገድ ኘሮጀክቱ 622.4 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል፡፡ የመንገድ ግንባታ ስራው በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ፣ የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ ፍሳሽ ቱቦ ቀበራና ማንሆል ሰራ እንዲሁም የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ሁለተኛው  ኮዬ ፈቼ ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሎት 1 የመንገድ ግንባታ ስራውን አይ.ኤፍ.ኤች ኢንጂነሪንግ የሚያከናውነው ሲሆን የማማከር ስራውን ዩናይትድ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እያከናወነው ይገኛል፡፡ የመንገድ ግንባታው 5 የአስፋልትና 27 የኮብል መንገዶች ሲኖሩት የአስፋልት መንገዶቹ በአጠቃላይ 4.3 ኪ.ሜትር ዝርመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 12/40 ሜትር የጐን ስፋት ይኖራቸዋል፡፡ የኮብል መንገዶቹ 14 ኪ.ሜትር ዝርመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 10/20 ሜትር የጐን ስፋት አላቸው፡፡

ለመንገድ ኘሮጀክቱ 711.7 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል፡፡ የመንገድ ግንባታ ስራው በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ፣ የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ ፍሳሽ ቱቦ ቀበራና ማንሆል ሰራ እንዲሁም የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ሶስተኛው ኮዬ ፈቼ ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኘሮጀክት 18 የመንገድ ግንባታ ስራውን  አይ.ኤፍ.ኤች ኢንጂነሪንግ የሚያከናውነው ሲሆን የማማከር ስራውን ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እያከናወነው ይገኛል፡፡ የመንገድ ግንባታው 8 የአስፋልትና 14 የኮብል መንገዶች ሲኖሩት የአስፋልት መንገዶቹ 7 ኪ.ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 15/40 ሜትር የጐን ስፋት ይኖራቸዋል፡፡

የኮብል መንገዶቹ አጠቃላይ 5  ኪ.ሜትር ዝርመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በአማካይ 10/15 ሜትር የጐን ስፋት አለው፡፡ ለመንገድ ኘሮጀክቱ 550.8 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል፡፡ በተመሳሳይ በዚህም ኘሮጀክት ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የመንገድ ፍሳሽ ቱቦ ቀበራና ማንሆል ሰራ እንዲሁም የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡

እነዚህ የመንገድ ኘሮጀክቶች ግንባታቸው ሲጠናቀቅ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ምቹና የተሟላ የመንገድ አቅርቦት ስለሚፈጠር የተሻለ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ የሚኖራቸው ይሆናል፡፡(አ/አ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top