Connect with us

የአሁኑ የካርቱም ዘፈን ፤ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” ከሚለው ይለያል፡፡

የአሁኑ የካርቱም ዘፈን ፤ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” ከሚለው ይለያል፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የአሁኑ የካርቱም ዘፈን ፤ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” ከሚለው ይለያል፡፡

የአሁኑ የካርቱም ዘፈን ፤ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” ከሚለው ይለያል፡፡

 (እስክንድር ከበደ)     

ከሱዳን ዳርፉር የሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ፤ የሱዳን መንግስት ግፊት እንዲያደርግ ግብጽ አታደርገውም አይባልም፡፡ ሰላም አስከባሪው ከአካባቢው  እንዲለቅ የተፈለገው ያለምክንያት አይደለም፡፡ የሰላም አስከባሪው አባላትን በብዛት ያዋጣችው ኢትዮጵያ በመሆኗ፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር ቢሆኑም የሱዳንና የግብጽ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መታዘባቸው አይቀርም፡፡ 

ግብጽ ወታደራዊ ባለሙያዎች ፣ጠበብትና  ተዋጊዎች  የሱዳንን ”ወታደራዊ ዩኒፎርም”(ህግ ማስከበሩ ዘመቻ መካሰስን እንደመነሻ ወስደን)  ለብሰው በዳርፉር ምድርና በሌሎች የሱዳን ስፍራዎች ምድብ (የአየር ኃይልን ጨምሮ ) ከፍተው ኢትዮጵያን ለማጥቃት አያስቡም ማለት አይቻልም፡፡

የሰላም አስከባሪው ሰራዊት ሱዳን ምድር ውስጥ እያለ  ግብጽና ሱዳን ሴራቸውን መፈጸም ይከብዳቸዋል፡፡በዳርፉር ብጥብጡ ቢነሳና ሌሎች የሱዳን ኃይሎች በሱዳን መንግስት ፈተና በቢሆኑ  በሱዳን ግብዣ  የግብጽ  ወታደሮች ወደ ዳርፉር  ሊገቡም ይችላሉ፡፡

 በህግ ማስከበሩ ዘመቻ የኤርትራ ወታደሮች  ወደ ትግራይ ክልል ገብተዋል በማለት የአረቡ ጸሀፊያንና የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሀን ፍንጭ ለማግኘት ወይም በመላምት የሚጽፉበት  ከጀርባው ከበደ ያለ ምክንያት እንዳለው መጠርጠር ያስፈልጋል፡፡ ኤርትራ ኢትዮጵያን አግዛለች በሚል ግብጾች ከሱዳን ጋር ለማበር ጠንካራ ማስረጃ ፍለጋ ይመስላል፡፡

የተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪ ከሱዳን መውጣት ለሱዳን መንግስትና ህዝብ የሚፈጥረው በኢኮኖሚም ሆነ  የጸጥታ ማስከበር  የሚፈጥረው ጫና ይታወቃል፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 የተካሄደው የእስራኤል ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የግብጹ ፕሬዚዳንት ጋማል አብዱናስር የመጀመሪያ ጥያቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ጦር ከመካከለኛው ምስራቅ እንዲወጣ  ነበር፡፡

ግብጽና ሳኡዲአረቢያ የመሩት የገልፍ አገራት  በኳታር ላይ  እ.ኤ.አ በ2017 ሰኔ ወር ላይ  በድንገት የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማአቀብ እንደጣሉ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ኤርትራና ጂቡቲ የሚወዛገቡበትን የራስ ዱሜራ( እኔ ለአትዮጰያም የሚገባ ብዬ የማስበው ስትራቴጂክ ቦታ) የኳታር 800 ወታደሮች ለቀው በመውጣታቸው ኤርትራ ወዲያው ተቆጣጥረውታል፡፡ 

ኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማአቀብ ለማስነሳት በሚያደርጉት ጥረት ጂቡቲ ኤርትራ ራስ ዱሜራን ይዛብኛለች ብለ እሪ ማለቷ ይታወሳል፡፡ ይሄኔ አብይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ዶክተር ወርቅነህና የሱማሊያን ልኡካን ወደ ጂቡቲ ልከው  የጂቡቲን ተቃውሞ አለዝበዋል፡፡ እናም ኤርትራ ማእቀብ ተነሳላት፡፡

ሰሞኑን ሳኡዲአረቢያ መራሹ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ከኳታር ጋር እርቅ ለማድረግ የተለሳለሰ አቋም መያዛቸው ተስምቷል፡፡ የግብጽ አንድ እርምጃ በብዙ መለኪያዎች የምንመዝንበት ጊዜ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ካይሮ የአባይን ወንዝ ጉዳይ የቼዥ ጫዋታ ካደረገችው ቆይታለች፡፡ እያንዳንዱ ጠጠር የምትገፋው በጥንቃቄ ነው፡፡ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፡፡

ከሱዳን ጋር አብረን በሱዳንኛ ድሮም ዘፍነናል፡፡ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” በአረብኛ ቅላጼ አማርኛ የዘፈነው ዘፋኛቸውን የአሁኖቹ ያውቁታል ብለን ከተኛን ሀገርን አስይዘን ከመቆመር አይተናነስም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

 • “ዛቻ!!” የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ ! “ዛቻ!!” የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

  ነፃ ሃሳብ

  “ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

  By

  “ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ ! (ንጉሥ ወዳጅነው – ድሬቲዩብ)  ለማንኛውም አለመግባባት ዘመናዊው መፍትሄ መነጋጋርና መደራደር...

 • ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው

  ነፃ ሃሳብ

  ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው

  By

  ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው “አንጋፋ” የሕይወት ዘመን ሽልማት ቦርድ፣ የሚከተሉትን የሽልማት መሣፍርት እንደ መነሻ በመያዝ ነበር ተሸላሚዎችን...

 • መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡ መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡

  ባህልና ታሪክ

  መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡

  By

  መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡ ****** (ተጓዡ ጋዜጠኛ...

 • የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት

  ባህልና ታሪክ

  የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት

  By

  የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት (ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የወርሃ ሚያዚያ ኩነቶችን ከታሪካችን ትዝታዎች እየጨለፈ እስከ...

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

To Top