Connect with us

ብልጽግና እና ህወሓት ምንና ምን ናቸው?

ብልጽግና እና ህወሓት ምንና ምን ናቸው?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ብልጽግና እና ህወሓት ምንና ምን ናቸው?

ብልጽግና እና ህወሓት ምንና ምን ናቸው?

(እሱባለው ካሳ)

 የህወሓት ጎምቱዎች ተያዙ፣ ተደመሰሱ የሚለው ዜና  ብዙዎችን አስደስቷል፡፡ እንደህወሓት ያለ የሕዝብ ጠላት መደምሰስ ማስደሰቱ ክፋት አልነበረውም፡፡ ግን ያልተመደሰሱ የህወሓት ራዕይ አራማጆች፣ በምግባርም በመልክም የህወሓት ልጆችን በጉያ ይዞ ብዙ መናገር በከንቱ ጉንጭን ማልፋት ነው፡፡

ህወሓቶች ለምን በሕዝብ ተጠሉ? በአጭሩ ከሕዝቡ ፍላጎትና አስተሳሰብ ተቃርነው በመቆማቸው ነው፡፡ “እንመራሃለን” የሚሉት ሕዝብ ጠላት ሆነው በመታየታቸው ነው፡፡ በጥጋብ መንፈስ ውስጥ ሆነው ጭቁኑን ሕዝብ አብዝተው በመናቃቸው ነው፡፡

የሕዝቡን አንድነት ይፈራሉ፡፡ እናም ሕዝቡን በዘርና በጎሳ ከፋፍለው እንዳይተማመን አደረጉት፡፡ አንድ ብሔር ለይተው “ነፍጠኛ”፣ “ጨቋኝ ገዥ መደብ” እያሉ ሲያጥላሉት፣ ከሌሎች ጋር ሲያባሉት ኖሩ፡፡ 

የአይን ቀለሙ ያላማረቸውን ሁሉ በጠላትነት መፈረጅና ማሳደድ የህወሓቶች ልዩ መለያ ነበር፡፡ በሃይማኖት ጉዳዮች ገብተው ሲፈተፍቱ  ” ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው፣ አንዱ በሌላው ጣልቃ አይገባም” ብለው የጻፉት ሕገመንግስት እንኳን አላገዳቸውም፡፡

ሌላው ቀርቶ በየዓመቱ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እያሉ ብዙ በጀት እየመደቡ የሚያከብሩት በዓል ከጭፈራ ያለፈ እርባና ያለው ቁምነገር ሳይታይበት ዓመታት የነጎዱት ታስቦበት ነው፡፡

 አገዛዛቸውን በዘመድ አዝማድ፣ በትውውቅ፣ በዘርና በጎሳ ላይ መስርተው ሀገሪትዋን ከመጋጥ አልፈው ብዙሀኑን የበይ ተመልካች አደረጉት፡፡ ሙስናና ሌብነት መደበኛ ስራ አደረጉት፡፡ በስልጣን መባለግ መለያቸው ሆነ፡፡ የተቃወማቸውን ብቻ ሳይሆ ገና ለገና ሊቃመወን ይችላል ያሉትን ሁሉ እያጋዙ አሰሩ፡፡ አሳደዱ፡፡ አንዳንዱንም ገደሉ፣ በእስር ቤት ኢ ሰብኣዊ ግፍም ፈጸሙ፡፡

የፓርቲ ተለጣፊ የሆነና ኢንዶውመንት የሚባሉ ኩባንያዎችን ቀፍቅፈው ሕጋዊ ነጋዴውን ከጨዋታ ውጪ አደረጉት፡፡ ኩባንያዎቹ ከፍተኛ ትርፍ የሚዝቁ ቢሆኑም ገንዘቡ የትና ለምን አላማ እንደሚውል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በአግባቡ ኦዲት ተደርገው ስለማወቃቸውም አይታወቅም፡፡

ዛሬስ? ምን አዲስ ነገር አለ? ከኢህአዴግ የተፋታው ብልጽግና የቀድሞ የህወሓት/ኢህአዴግ መስመር የቱን ያህል ተላቋል? የዜጎች  መብት እየተከበረ ነው ወይ? ዜጎች በፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ብቻ የመሳደዳቸው፣ለእስር የመጋዛቸው ጉዳይ የተዘጋ ፋይል ሆኗል ወይ? ስራ ለመያዝ፣ የተሻለ መንግስታዊ አገልግሎት ለማግኘት ትላንት ትልቅ መስፈርት የነበረው የዘር ካርድ ዛሬ ማስቀረት ተችሏል ወይ?

የዜጎች የእምነት ነጻነት፣ ሃይማኖታዊ ክብረበዓላቸውን በመረጡት አካባቢ በሰላም የማክበር መብታቸው ተረጋግጧል ወይ? ዜጎች በመረጡት አካባቢ ሀብት የማፍራት፣ የመኖር፣ የመንቀሳቀስ መብታቸው የተከበረ ነው ወይ?

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች የሚገኙ ኢንዶውመንት ድርጅቶች የት ነው ያሉት? ምን እየሰሩ ነው? ከበፊቱ ምን የተለየ አካሄድ ይዘዋል?

መንግስታዊ ሙስናው፣ ከገቢ በላይ ሐብት አፍርቶ በአደባባይ እዩኝ፣ እዩኝ ማለቱ፣መንጎማለሉ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

 የብልጽግና ፖለቲከኞች ከህወሓት በተለየ ምን እየሰሩ ነው? ሕዝብን ወይንም  አንድ ብሔርና ቡድን እንደህወሓት “ነፍጠኛ”… መፈረጅ፣ ማሸማቀቅና ጥላቻ ማቀጣጠል ታርሟል ወይ? ሰዎች በገዛ ሀገራቸው መርጠው ባልተወለዱበት ብሔር እንደጠላት ታይተው ለጥቃት የሚጋለጡበት አሳፋሪ ክስተት በአስተማማኝ መልኩ ማስቆም ተችሏል ወይ? አጥፊዎችን በፍጥነት ለይቶ ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ዜጎችን በሚያሳምን መልኩ መተግበር ተችሏል ወይ?

የብልጽግና ሰዎች ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎች ጥርት ያለ መልስ በመስጠት ውስጣቸውን ከህወሓት ራዕይ አስፈጻሚዎችና የህወሓት ቫይረስ ተሸካሚዎች ማጽዳት ካልቻሉ አሁንም ሀገራችን በእጅ አዙር በህወሓት የሙት መንፈስ መመራትዋ አይቀሬ ይሆናል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

 • “ዛቻ!!” የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ ! “ዛቻ!!” የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

  ነፃ ሃሳብ

  “ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

  By

  “ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ ! (ንጉሥ ወዳጅነው – ድሬቲዩብ)  ለማንኛውም አለመግባባት ዘመናዊው መፍትሄ መነጋጋርና መደራደር...

 • ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው

  ነፃ ሃሳብ

  ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው

  By

  ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደፃፈው “አንጋፋ” የሕይወት ዘመን ሽልማት ቦርድ፣ የሚከተሉትን የሽልማት መሣፍርት እንደ መነሻ በመያዝ ነበር ተሸላሚዎችን...

 • መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡ መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡

  ባህልና ታሪክ

  መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡

  By

  መቅደላ በሚያዚያ፤ አምባ ላይ የወደቀው የጀግና ደም ፍሬ አፍርቶ እልፍ ሆኖ አድዋ የበቀለበት፡፡ ****** (ተጓዡ ጋዜጠኛ...

 • የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት

  ባህልና ታሪክ

  የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት

  By

  የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት (ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የወርሃ ሚያዚያ ኩነቶችን ከታሪካችን ትዝታዎች እየጨለፈ እስከ...

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

To Top