Connect with us

በአንኮበር የዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየምና የባሕል ማዕከል ተመረቀ

በአንኮበር የዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየምና የባሕል ማዕከል ተመረቀ
አብመድ

ባህልና ታሪክ

በአንኮበር የዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየምና የባሕል ማዕከል ተመረቀ

በአንኮበር የዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየምና የባሕል ማዕከል ተመረቀ

የዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየምና የባሕል ማዕከል የሚገኘው በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ከተማ በአንኮበር ነው፡፡ በ333 ዓ.ም  የተመሠረተችው አንኮበር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የበርካታ ነገሥታት መቀመጫ እንደነበረችና ሌሎች ነገሥታትም ከሌላ አካባቢ ወደ አንኮበር መጥተው ንግሥናቸዉን ሲቀበሉ እንደነበረ የአንኮበር ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

አንኮበር ከተቆረቆረች ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ የሸዋ ነገሥታት መቀመጫ በመሆን አገልግላለች። 38 ነገሥታትም ነግሰውባታል። ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህም አምሀየሱስ፣ አስፋው ወሰን፣ ወሰን ሰገድ፣ ሳኅለስላሴ፣ ኀይለመለኮትና ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነግሰውባታል። መቀመጫቸው አድርገዋትም ሀገር አስተዳድረዋል።

ይህች  የጥንታዊ ነገሥታት መቀመጫ የበርካታ ባሕላዊ  ትውፊቶችና ታሪካዊ እንዲሁም  ሃይማኖታዊ  ቅርሶች መገኛ ናት።

የወረዳው ባሕልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኀላፊ ፈለቀ ምሕረት  ለአብመድ እንደተናገሩት ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ የወርቅ ጽናጽል፣ የብር ከበሮ እና መቋሚያን ጨምሮ በወቅቱ  የነገሥታቱ መገልገያ የነበሩ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች መገኛ ናት።

እነዚህን ቅርሶች በተደራጀ ቦታ ለማስቀመጥና ለጉብኝት ክፍት አልነበሩም፣ ይልቁንም የተቀመጡት በወረዳው በሚገኙ 97 ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ተበታትነው ነበር። በዚህም ምክንያት ቅርሶችን ከነታሪካቸው በሚፈለገው ደረጃ ለትውልድ ማስተዋወቅ አልተቻለም ብለዋል።

ወረዳውም በቱሪዝም ተጠቃሚ መሆን አልቻለም ነው ያሉት። አሁን አንኮበር ታሪኳን የምታስተዋውቅበትና ቅርሶቿንም የምታድስበት ዘመናዊ ቤተመዘክር እንደተገነባላት አስረድተዋል።

እንደ ኀላፊው ገለጻ ወረዳው  ለቤተ መዘክሩ ግንባታ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎበታል። ቤተ መዘክሩ የደኀንነት ካሜራዎች ተገጥመውለታል። የክልሉ መንግሥትም  ቅርሶች ከሰው ንክኪ ነፃ  ሆነው እንዲጎበኙ የሚያስችል መስተዋት አሠርቷል።

ይህም ቅርሶች ለጉብኝት ክፍት እንዲሆኑ ከማስቻል ጀምሮ ደኀንነታቸው በአስተማማኝ መልኩ እንዲጠበቅ ያደርጋል ብለዋል። የወረዳውን የቱሪዝም እንቅስቃሴም በከፍተኛ ደረጃ  ያነቃቃል ተብሎ ታምኖበታል። ወረዳውም ቱሪዝሙን ይበልጥ ለማነቃቃት  በቤተ መዘክሩ አጠገብ ደረጃውን የጠበቀ የእንግዶች ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሯል።

(ደጀኔ በቀለ- አብመድ)

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top