Connect with us

የፓለቲከኞችና የአክቲቪስቶች የአዕምሮ ጤና ጉዳይ !

የፓለቲከኞችና የአክቲቪስቶች የአዕምሮ ጤና ጉዳይ !
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የፓለቲከኞችና የአክቲቪስቶች የአዕምሮ ጤና ጉዳይ !

የፓለቲከኞችና የአክቲቪስቶች የአዕምሮ ጤና ጉዳይ !

(ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ )

ከሁነቶች በዘለለ የነገሮችን ተደጋገሚ መልክና ባህሪ (pattern) በአግባቡ መረዳት፣ እንዲሁም ክስተቶችን የወለዷቸው የአዕምሮ ጤና ሁኔታና ውቅር መገንዘብ ስለ አገራችን የፓለቲካ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው የተሻለ መረዳት እንዲኖር ያግዛል።

ከዚሁ አንፃር ፓለቲከኞቻችንና አክቲቪስቶቻችን ተደጋጋሚ የሚያሳዩትን ባህሪያትንና የባህሪይ ችግሮችን ከሚወስኑ መሰረታዊ ግን በማህበረ—ፓለቲካ ተዋስኦዎቻችን ውስጥ በቂ ትኩረት ያልተሰጠው የአዕምሮ ጤና ጉዳይ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝና በቂ ጥናትና ምርምር ቢደረግበት ለአገራዊ ችግሮቻችንም ዋነኛ አስረጂ ሆኖ መቅረብ የሚችል ይመስለኛል።

ዛሬ ዛሬ በግልጽ የሚታየውና በትኩረት ካልተሰራበት አገራችንን አሁን ካለችበት በላይ ወደ ከፋ ችግር ሊወስዳት ከሚችሉ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የአዕምሮ ጤና ሁኔታቸው ችግር እንዳለባቸው በግልጽ የሚታዩ ፓለቲከኞቻችን (በገዢውም፣ በተቃውሞውም)ና አክቲቪስቶች ውስጥ የሚታየው አሳሳቢ የአዕምሮ ጤና መጓደል ነው።

በተደጋጋሚ ከምናያቸው የፓለቲከኞቻችን የአዕምሮ ጤና መታወክ ማሳያ ችግሮችና ባህሪያቶች ውስጥ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል፦

1) በቀላሉ ያሚታዩ ሀቆችን አዛብቶ መተርጎም፣ በተለያዩ ጊዜ የሚቃረኑ ሀሳቦችንና አላማዎችን መያዝ (schizophrenic symptom)፣

2) ከፍተኛ የሆነ የስሜት መረበሽና ያለመረጋጋት (መረበሹ በሚዲያ ሰዎች በግልጽ እስከሚረዱት ድረስ የሚታይ)፣

3) ከፍተኛ የሆነ የጭንቀትና የድብርት ስሜት፣ በከፍተኛ የሱስ ስሜት ጡዞ አደባባይና በሸንጎ መቅረብ፣

4) ተደጋጋሚና የህመም የሚመስል ውሸት፣ የፈጠሩትን ውሸት ሌሎች እንዲቀበሉት መጣር፣

5) insecured የመሆን፣ ከልክ ያለፈ ተጠራጣሪነት፣ ከልክ ያለፈ ጀብደኝነት፣

6) ሌሎች ያጠቁኛል ወይም ይጎዱኛል ብሎ ከልክ በላይ መጨነቅና ፍርሃት፣

7) የተጋነነ የራስ ምስል፣ የተወሳሰበ የበታችነትና የበላይነት ስሜት

8) በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት የመፈለግ፣ ተለዋዋጭ የጨለምተኝነትና የሚዋዥቅ የቀቢፀ ተስፋ ስሜት ፣

9) ከጉዳት በኋላ የሚከሰት ጭንቀትና የስሜት ዝብርቅርቅ (PTSD)፣

10) ለሌሎች የመረረ ጥላቻ ወዘተ… በስፋት እንደሚንፀባረቅ ይሰማኛል።

በዚህ የአዕምሮ ጤና ሁናቴ ውስጥ ሆነው በሚወሰኑ ውሳኔዎች ስንት የአገራችን ምስቅልቅሎች እንደተፈጠሩና በቀላሉ በውይይት ሊቀረፉ የሚችሉ ችግሮች አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ዋጋ እንዴት እንዳስከፈለ ለመረዳት የትህነጋዊያንን የመጨረሻ ሰዓት የእብደት ውሳኔና ድርጊት ማየት ብቻ በቂ ነው።

ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቡና መረበሽና የአዕምሮ ጤና መታወክ ይታይባቸው የነበሩ ትህነጋዊያንና ኦነጋዊያንም ፓለቲከኞች አገራችንን በደም አላባ እንድትታጠብ ማድረጋቸውን ስናስብ፤ እንዲሁም ዛሬም ድረስ በኦሮሞ «ብልጽግና» ውስጥ ያሉ ስሜታቸው የታወከ፣ የአዕምሮ ጤና ሁኔታቸው በግልጽ በሚታይ ደረጃ ችግር ያለባቸው፣ ከነሱ አመለካከትና ፍላጎት ውጪ የሆነ ሀሳብ ያረመደ የመሰላቸውን ሁሉ እየተንደረደሩ የሚዋጉ ግለሰቦችን በብዛት ስናይ፣ በቀጣይም ለአገራችንና ለህዝባችን ከትህነግ የከፋ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ አደገኛ ግለሰቦችና ቡድኖች መኖራቸው ግልጽ ይሆንልናል።

የችግሩን ግዝፈት የሚያሳየው ደግሞ የነዚህ ግልገል ፋሽስቶች የአዕምሮ ጤና መታወክ ባለሙያ ያልሆነ እንደኔ ያለ ሰው ጭምር ሊገነዘበውና ሊያየው በሚችል ደረጃ ፈጦ መታየቱ ሲሆን ይህም ጉዳዩን በጣም አሳሳቢ ያደርገዋል።

የአርባጉጉ፣ በደኖ፣ እንቁፍቱ፣ ወተር፣ አሰቦት ገዳም፣ ሀረር፣ ባሌ ጎባ፣ ባሌ ሮቤ፣ አሳሳ፣ አሰላ፣ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ መተከል፣ ጉራ ፈረርዳ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጉሊሶ፣ ማይካድራ፣ ወለጋ… ወዘተን ለመሳሰሉ ማንነትን የለዩ እልቂቶች፣ ጭምላ ጭፍጨፋዎች፣ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀሎች መፈጠር ከፓለቲካ ስርዓታችን ብልሹነት ባልተናነሰ የተዋናዮችና የአስፈፃሚዎች የአዕምሮ ጤና ሁኔታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መገመት ይቻላል።

ችግሩ ከግለሰቦች አልፎ ወደ የጋራ ወይም የቡድን የአስተሳሰብ ዝንፈትና መለያ ባህሪ ወደመሆን ሲደርስ «የጋራ እብደት/የጋራ ስካር» ወይም collective narcissism ተብሎ በስነ ልቦና ባለሙያዎች ይጠራል። የጋራ እብደት ወይም የጋራ ስካር ውስጥ ያለ ቡድን ደግሞ እንደትህነግ እስኪጠፋ ድረስ የሚያደርገውን አያውቅም።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

To Top