Connect with us

“የህወሓት ጁንታ በብሔር ስም ብዙ ሸፍጥና ተንኮል ሰርቷል” የኢዜማ ሊቀመንበር

"የህወሓት ጁንታ በብሔር ስም ብዙ ሸፍጥና ተንኮል ሰርቷል” የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ
Ethiopian press agency

ዜና

“የህወሓት ጁንታ በብሔር ስም ብዙ ሸፍጥና ተንኮል ሰርቷል” የኢዜማ ሊቀመንበር

“የህወሓት ጁንታ በብሔር ስም ብዙ ሸፍጥና ተንኮል ሰርቷል” የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ 

የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ በወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ የጁንታውን ሴራና በደሎች ዘርዝረው አስረድተዋል

ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር ብሄረሰቦች የተፈጠሩት ቡድኑ ከመፈጠሩ ከሚሊዮን ዓመት በፊት ነው፤ ጁንታው ግን የብሄር ብሄረሰቦች ፈጫሪ መስሎ ታይቷል፤ ህዝቦቹ የነበሩና የሚኖሩ ናቸው፤

ቡድኑ ጉራጌን ከስልጤ፣ አማራን ከኦሮሞ፣ ወላይታን ከሃድያ፣ ሱማሌን ከኦሮሞ፣ አፋርን ከኢሳ፣ አማራን ከትግሬ ወዘተ አጋጭቶ እያስታረቁ ለመኖር ብሄረሰብን የስልጣን መወጣጫ ነው ያደረገው፤

ቡድኑ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት አከብራለሁ እያለ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ሲጥስ የኖረ ነው፤

ብሄር ብሄረሰብን ለስልጣን መወጣጫ እንጂ ጥቅምና መብትን ለማስከበር እንዳልቆመ የሚያሳዩ ብዙ ነገሮች አሉ፤

ብሄረሰቦች የኖሩበትን ቀመር ‹‹እኔ ብቻ ነኝ›› የማውቀው ሲል ቢኖርም ብሄር ብሄረሰቦች አንቅረው ተፍተውት ከአዲስ አበባ ሮጦ በመሄድ መቀሌ ለመሸሸግ ሞክሯል፤

ቡድኑ መኖሪያ ወይም የአገዛዝ ስበቡ ለብሄር ብሄረሰቦች ቁሜያለሁ የሚል ነው። እውነተኛ ማንነቱ ግን ክህደትና የአገር ሃብት መዝረፍ ነው፤

ቡድኑ ስልጣን ከያዘ በኋላ በትጥቅ ትግል ላይ እያለ በ1967 እና 68 የቀረጸውን ርዕዮተ ዓለም (ማንፌስቶ) ወደ ተግባር ለመቀየር የሄደበት ርቀት አለ፤

በማንፌስቶው ታላቋ ትግራይን እመሰርታለሁ የሚለው ቅዠት ቢኖረውም ከመሰረቱ የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም።

ቡድኑ መግደልና ትልልቅ ሰዎችን እንዲሁም ተቀባይነት ያላቸውን ሰዎችን ማጥፋት የጀመረው ትግራይ ውስጥ ነው፤

ቡድኑ የቆመበትን፣ የተወለደበትን፣ የወጣበትን አካባቢ ማውደምና አቅም ስላልነበረው ታላቋን ትግራይ እንዳትመሰረት ሆኗል፤

እንደ ህወሓት አይነቱ እብድ ቡድን ትልቁን ጃንጥላ ቀዶ ትንንሾችን ሰፈር መመስረት እንደማይችል ፍጹም ማሳያ ነው፤

የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች እህትና ወንድሞቹ ጋር በመሆን የመሰረተ ህዝብ ነው፤ ስለዚህ ቤቱን እያፈረሱ መከታው ነኝ ማለት አይቻልም፤

የኢሕአዴግ ፕሮግራም በተወሰነ ደረጃ ህገ መንግስቱ ላይ ተንጸባርቋል። ስለዚህ ከራሱ ማንፌስቶ ተነስቶ እስከ ህገ መንግስት ውስጥ ማካተት ደረጃ ደርሷል።

በፓርቲ ደረጃ ከተሄደም በአቶ መለስና በህወሓት፣ በሕወሓትና በኢሕአዴግ፣ በኢሕአዴግና በመንግስት መካከል ምንም የሚያለያይ መስመር አልነበረም አቶ መለስ ሲያስነጥስ ታች ያለውም ካድሬ ሲያስነጥስ ኖሯል፤

በማንፌስቷቸው መሰረት ህግ ከማርቀቅ ጀምሮ ህገ መንግስት እስከማድረግ ጫፍ ድረስ የሄዱበት፣ ፓርቲና መንግስትን የማይለያይበት አድርገው የሰፉበት፣ እነርሱ ከሌሉ አገር አይኖርም እስከማለት የደረሱ ጉዶች ነበሩ፤

አሃዳዊ ስርዓት ልክ እንደነውር የሚቆጥሩ አንዳንድ ደነቋቁርት አሉ፤ ፌዴራላዊ ማለት ዲሞክራት ማለት አይደለም፤ አሃዳዊ ማለትም አምባገነን ማለት አይደለም፤ ሁሉም የአስተዳደር ስርዓት ነው፤

የህወሓት ስርዓት ለንጉሳዊ የቀረበ ነው፤ በ27 ዓመታት የኢህአዴግ አስተዳደር ዘመን አራት ወይም አምስት ክልሎች በሞግዚት ነበር ሲተዳደሩ የነበሩት፤

አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላና ሐረር ክልሎች ለአቅመ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አልደረሳችሁም ተብለው ተገፍተረው ነበር። እነዚህ ክልሎች በአገሪቱ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን እኩል ከህብረተሰቡ ጋር ነበር የሚሰሙት፤

ይሄንን የሚያክል ህዝብ ከጨዋታ ውጭ አድርገው ፌዴራላዊ ሰርዓት ነበር ማለት ቀልድ ነው፤

የፌዴራል ስርዓት በወሬና በወረቀት ላይ ካልሆነ በስተቀር በፍጹም አልነበረም። እንደውም ምልክቱም አልታየም፤

ፓርቲዎችን በሴራ ለሁለትና ለሶስት እየከፈለ ክፋዩን በገንዘብ በመደለል ሞግዚት ፓርቲዎችን እያስቀመጠና ሰርጎገቦችን እያደራጀ እያስገባ ፓርቲዎችን እየበተነ ኢትዮጵያ ውስጥ አማራጭ ፓርቲ እንዳይኖር አድርጎ ቆይቷል፤

የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ብለው ሌባ ሰብስበው ገንዘብ እየረጩ አገር ልናቀና ነው በማለት የሄዱበት ርቀት የኢትዮጵያን ህዝብ ልክ አለማወቅ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የአፍሪካ ብቻ አይደለም የመላ ዓለም የጥቁር ህዝቦች ኩራት ነው፤

የህወሓት አመራሮች በጣም ብዙ ዓመት በፖለቲካ ውስጥ ኖረዋል፤ ጥርሳችንን የነቅለንበት ነው ይላሉ፤ ነገር ግን ፖለቲካ አያውቁም፤

መንግስት በአሁኑ እርምጃ ዋነኞቹን ጥጋበኞች ልክ ስላስገባና ስላስተማረ ከዛ በኋላ ያለው መለስተኛ ጥጋበኞች ስርዓት ወይም አደብ ይገዛሉ ብዬ አምናለሁ፤

በማይካድራ የኢትዮጵያን እምነትን፣ ባህልንና ሃይማኖትን የማይመጥን ፍጹም ነውር የሆነ ስራ ተፈጽሟል፤

(ኢ ፕ ድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top