Connect with us

የሱዳን ሠራዊት ወረራ በተመለከተ

የሱዳን ሠራዊት ወረራ በተመለከተ
የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር

ዜና

የሱዳን ሠራዊት ወረራ በተመለከተ

የሱዳን ሠራዊት ወረራ በተመለከተ

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው  የሰጡት መግለጫ ፦

ዞናችን ባሳለፍናቸው ወራት  አንፃራዊ የሆነ ሰላምና መረጋጋት ተፈጥሮ ህዝባችን ወደልማቱና የእለት ከለት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ተመልሶ በርካታ ተግባሮች እያከናወነ መቆየቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጅ ከሀዲው ና የእናት ጡት ነካሹ የትነግ የጥፋት ሀይል  የሀገራችን አርማና መለያ በሆነው በሰራዊታችን ላይ የፈፀመውን ወንጀል ተከትሎ  ህግና ስርዐት ለማስከበር የተከበረው የዞናችን ህዝብ፣ ልዩ ሀይልና ሚሊሻችን ከሰራዊታችን ጋር ተሠልፎ አኩሪና አንፀባራቂ ድል አበርክቷል።

በጥፋት ቡድኑ ላይም ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ  አገራዊ ተልኮውን በመወጣት የጎላ ድርሻ አበርክቷል እያበረከተም ይገኛል ።  ይሁን እንጅ ዞናችን  የጁንታውን የጥፋት ተልእኮ  ለመከላከል የፀጥታ ሀይላችን  ወደግዳጅ ሲንቀሳቀስ  ወንድም ከሆነው የሡዳን ህዝብና መንግስት  የሚያዋስኑ  ደንበርና አካባቢዎችን የተተወው ደጀን ለሆነው  ለሱዳን ህዝብና መንግስት ነበር ።

ዳሩ ግን ምንም እንኳ የሱዳን ህዝብና መንግስት ሙሉ ዕምነትና ፍላጎት ነው ብለን ባናምንም  በአንዳንድ የሱዳን ሰራዊቱ አመራርና የሌላ ተልእኮ ሴራ ፈፃሚ አካላት  በዳግም ከሀዲ ቡድን ዱላ አቀባይነት  ሰራዊታችን ሲጠብቃቸው የነበሩ ቀጠናና ካንፖችን  ተሻግሮ  በመግባትጥፋት በመፈጸም ላይ ነው።

ከ27/2/2013 ጀምሮ እስከ 18/4/13 ማለትም  እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከ180 እስከ 200 የሚሆኑ የዞናችን አርሶ አደሮች የእርሻ ካንፕ የመውረር ፣የማቃጠል፣ንብረት የመዝረፍ፣ ህይወት የማጥፋትና ባልተለመደ ሁኔታ  በርካታ መካናይዝድ ጦር በማዝመት በሞርተር፣ዙ 23ና መድፍ ቀጠናውን  በማወክ በተስፋፊነት ስሜት  በርካታ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በዚህም  በአርሶ አደሮቻችን  ካንፕ ለዘመናት የተከማቹ የእርሻ  ማሽነሪዎች፣ሰብል ና እንስሳት  ሳይቀር እየዘረፈና እያቃጠለም ይገኛል።  ዜጎችንም በማንነታቸው እያሠረና እያንገላታ ነው ።

በጉዳቱም ከ1ቢሊዬን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ተዘርፏል  ዘረፋና በቃጠሎ ወድሟል።   ከ450 እስከ 500በለይ የሚሆኑ አባውራና እማውራ ከ1750 በላይ የሰላም በር ቀበሌ ህዝቦች ተፈናቅለዋል። ሰፈራቸውም እየተቃጠለ ይገኛል ። 

ይህ ጉዳት ሲፈፀም የተከበረው የዞናችን ህዝብ ወንድም ለሆነው የሱዳን ህዝብና መንግስት ካለው ክብር፣  አብሮ የመኖርና  የሰላም ፍላጎት በመነጨ እና   የሀገራችን መንግስትና ህዝብ ያሉትን የሰላም አማራጮች ሁሉ አሟጦ የመጠቀም ጥረቱን በመረዳት   በሆደ ሰፊነት ነገሮችን እየተመለከተ ነው።

ሆኖም ግን የሱዳን ሰራዊት  በውስጡ ከተሰገሰጉ ሴረኞች ተልኮ በመጎራረስ በየቀኑ  ጥፋት ከማድረሱም በላይ አሁንም  በቅርብ የሚገኙ ከተሞቻችን  በስጋት ላይ ናቸው ።

ስለሆነም በየደረጃው ያለ የመንግስት አካላት በተለይ ደግሞ የፌደራል መንግስት ይህን ተረድቶ  የሰላም አማራጭ በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የማይመጣ በመሆኑ  እየደረሰ ያለውን ጉዳት ግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል።

በመሆኑም  በፌደራል መንግስት በኩል በተጀመረው ሰላማዊና ድርድር  አማራጭ  ወይም ደግሞ  አስፈላጊው ህግ  የማስከበር  እርምጃ ተወስዶ የዞናችን ህዝብ  ያሳየውን ጭዋነት በመገንዘብ ከተጋረጠበት የሰላምና ደህንነት ስጋት ወጥቶ ወደ ቀደመው ሰላሙና ልማቱ እንዲመለስ  አስፈላጊው አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ  እንዲወስድ  እንጠይቃለን  ።

18/04/2013ዓ.ም

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር

ገንደውሃ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top