Connect with us

ዜጎች ህገ መንግስታዊ ነጻነታቸውን የሚያስከብሩበትን የፍትህ መድረክ ለመገንባት ወደ ኋላ የሚመልሰን የለም… ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ

ዜጎች ህገ መንግስታዊ ነጻነታቸውን የሚያስከብሩበትን የፍትህ መድረክ ለመገንባት ወደ ኋላ የሚመልሰን የለም… ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ
Ethiopian News Agency

ነፃ ሃሳብ

ዜጎች ህገ መንግስታዊ ነጻነታቸውን የሚያስከብሩበትን የፍትህ መድረክ ለመገንባት ወደ ኋላ የሚመልሰን የለም… ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ

ዜጎች ህገ መንግስታዊ ነጻነታቸውን የሚያስከብሩበትን የፍትህ መድረክ ለመገንባት ወደ ኋላ የሚመልሰን የለም… ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ

ዜጎች ህገ መንግስታዊ ነጻነታቸውን የሚያስከብሩበትን የፍትህ መድረክ ከመገንባት ወደ ኋላ የሚመልሰን ነገር አይኖርም ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ገለጹ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በነበራቸው ቆይታ በተለይም ባለፉት 2 አመታት ተኩል የተከሰቱ ሁከቶችና ጥቃቶች በሕወሃት ቡድን ስፖንሰርነት መካሄዳቸውንና ይህም በሚዲያዎቻቸውና በፖለቲካ መሪዎቻቸው በኩል በይፋ ድጋፍ ሲደረግበት ነበር ነው ያሉት።

በአማራና ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ልዩ ዞኖች ውስጥ ጸጥታ እንዲያስከበሩ የተሰማሩ ሃይሎችን እንዲመሩ የተላኩ ሃላፊዎች  ወደ መቀሌ በመጓዝ ትእዛዝ ተቀብለው ግጭቱ እንዳይረግብ ሲሰሩ እንደነበርም ለአብነት አስረድተዋል።

የፍትህ ዘርፉም ሆነ መንግስት የሚያካሂደው የተቋማት የለውጥ ግንባታ እዳይሳካ ጁንታው በተለይም በሚዲያው በኩል ግጭቶችን በማራገብ፣ በማሰራጨትና በመቀስቀስ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ ነበር ነው ያሉት።

ዶክተር ጌዲዮን እንዳሉት የህውሃት ቡድን ያካሄደውን የማደናቀፍ ተልዕኮ በመቋቋም በጸጥታና በፍትህ ተቋማት ላይ ቀስ በቀስ የተደረገው የለውጥ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚከሰቱ ሁከቶች እንዲቀንሱ በማስቻል ውጤት አስመዝግቧል።

“በሁለት አመታት ተኩል ውስጥ  በፍትህ ዘርፉ ከፍተኛ የሆኑ ጉዳዮች እያስተናገድንም ቢሆን እያንዳንዱን ሁኔታና የሚመጡ ማስረጃዎችን በመመልከት የፍርድ ሂደቶች ታይተው አብዛኛዎቹ ኬዞች እየተጠናቀቁ ነው” ብለዋል።

ረጅም ጊዜ የወሰዱና በየቦታው የሚታዩ ጉዳዮች መኖራቸው የፍትህ ሂደቱን እንዳረዘመው ገልጸው፤ “ እንደ እኛ አገር እጅግ ወስብስብና ሰፊ የሆኑ ጉዳዮች በሚያጋጠሙባቸው ያደጉ አገራት ነጻና ትልቅ አቅም ኖሮ እንኳን ከፍተኛ ጊዜ፤ በጀትና ሃለፊነትን የሚጠይቅ ነው” ብለዋል።

በጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኩል አብዛኛቹ ከአንድ ዓመት እስከ 2 ዓመት ያስቆጠሩ ጉዳዮች ብቻ መኖራቸውን አስታውሰው፤ እየተሻሻለ በሚመጣው የፍትህ ተቋሞች ጥንካሬ ከፍተኛ ለውጥ የሚታይ ይሆናል ብለዋል።

የፍትህ ተቋማትን የነጻነት ሂደት ከሚያረጋግጡት አንዱ የሆነውን ነጻና ገለልተኛ የፍርድ ሂደት ለማሳለጥ ባለፉት ሁለት ወራት አዳዲስ ዳኞች ወደ ስራ መግበታቸውንም አስታውቀዋል።

በቀጣይም ተቋማዊ ነጻነትን በማረጋገጥ ረገድ በሚከናወኑ ተግባራት “ዜጎች ህገ መንግስታዊ ነጻነታቸውን የሚያስከብሩበትን የፍትህ መድረክ ለመገንባት ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ የሚመልሰን ነገር አይኖርም” ነው ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ።

ተቋማት ራሳቸውን ችለው በነጻነት እንዲቀንሳቀሱ ማስቻል አስፈላጊ መሆኑን የጠቀሱት  ዶክተር ጌዲዮን፤ በለውጥ እንቅስቀሴው የሚዲያ ቋማት ነጻነትን የሚያስጠብቁ ፖሊሲ መዘጋጀቱ፣ በትግራይ ክልል በተቋቋመው አዲስ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብጠርን እንደምሳሌነት ጠቅሰዋል።

የሚመጣው ምርጫም ነጻነትን፣ እኩልናትንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ እንደሚሆንና የህግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እንደምትገነባም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።(ኢዜአ)

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top