Connect with us

ምርጫ ቦርድ አለመግባባት የፈጠሩት የኦነግ አመራሮች በጋራ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠሩ ወሰነ

ምርጫ ቦርድ አለመግባባት የፈጠሩት የኦነግ አመራሮች በጋራ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠሩ ወሰነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ነፃ ሃሳብ

ምርጫ ቦርድ አለመግባባት የፈጠሩት የኦነግ አመራሮች በጋራ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠሩ ወሰነ

ምርጫ ቦርድ አለመግባባት የፈጠሩት የኦነግ አመራሮች በጋራ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠሩ ወሰነ

(የቦርዱ ውሳኔ እነሆ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት መካከል የተፈጠረ አለመግባባትን አስመልክቶ የተሰጠ ውሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር አካላት መካከል ተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የተለያዩ አቤቱታዎች ሲደርሱት እንደነበር ይታወቃል፡፡

የፓርቲው የተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ አባላት ነሃሴ 01 ቀን 2012 ዓ.ም በተጻፈ እና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር በተፈረመ ደብዳቤ የድርጅቱን ሊቀመንበር መታገዳቸውን ለቦርዱ አሳውቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የድርጅቱ አመራር ላይ ተከታታይ  አቤቱታዎች አስገብተዋል፡፡

በሌላ በኩል የድርጅቱ ሊቀመንበር መስከረም 02 ቀን 2013 ዓ.ም ድርጅቱ ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እስከሚቀጥለው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሃላፊነታቸው ታግደው እንዲቆዩ እንደወሰነ ለቦርዱ አሳውቀዋል፡፡

ፖለቲካ ፓርቲ አባላት መኻከል አለመግባባት ሲከሰት እና ለቦርዱ አቤቱታ ሲቀርብለት በአዋጅ ቁጥር 1162/11 አንቀፅ 74 ንዑስ አንቀፅ 6 መሠረት ጉዳዩን ተመልክቶ የውሣኔ ሃሣብ የሚያቀርብ የባለሙያዎች ጉባኤ የማቋቋም ሥልጣን አለው፡፡ በህግ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ የሁለቱንም ቡድኖች ደብዳቤዎች እና አቤቱታዎች የሚያይ የባለሞያዎች ኮሚቴ ለማቋቋም ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት በእነ አቶ አራርሶ በኩል ባለሞያ ቢመድቡም ፣ በእነ አቶ ዳውድ በኩል ባለሞያ ለመመደብ ፍቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ የፓርቲው የውስጥ ደንብ መሰረት መጠናቀቅ ያለበት ጉዳይ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ ይህንን ጉዳይ ለማየት ፍቃደኛ የሆነ ባለሞያ ለማግኘት አልቻለም፡፡ በመሆኑም ቦርዱ በራሱ ጉዳዩን መርምሮ ለመወሰን ተገዷል፡፡

ቦርዱ ጉዳዩን በመመርመር ሂደት በሁለቱም ወገን ያሉ የፓርቲው አመራሮችን አነጋግሯል፡። ሁለቱም ወገኖች የጠቀሱት የፓርቲው ስነስርአት እና ቁጥጥር ኮሚቴንም ጠርቶ አወያይቷል፡፡ በውይይቱም ወቅት የፓርቲው ስነስርአት እና ቁጥጥር ኮሚቴ ከላይ በተጠቀሱ እግዶች ዙሪያ ውሳኔ መስጠት እንደማያስፈልገው ገልጿል፡፡ ከዚህም በመነሳት በአመራሮቹ መካከል ያለው አለመግባባት በፓርቲው ውስጥ እንደማይፈታ እና የቦርዱን ውሳኔ እንደሚፈልግ በመረዳት የሚከተሉትን ዋና ዋና ውሳኔዎች ቦርዱ ወስኗል፡፡

  1. ቦርዱ በድርጅቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አራርሶ ቢቂላ ፊርማ የተላከለትን የድርጅቱን ሊቀመንበር የታገዱበትን ስብሰባ የሚገልጸውን ቃለጉባኤ ተመልክቶ በቃለጉባኤው ላይ የተገኙት ስራ አስፈጻሚ አባላት ከስምንቱ  አምስት መሆናቸውን ከአምስቱ መካከልም አንዱ አባል ከዚህ ቀደም በዜግነታቸው የተነሳ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የተቀነሱ በመሆናቸው ስራ አስፈጻሚው ስብሰባ የሚጠበቀውን 2/3ተኛ መልአተ ጉባኤ ያልተሟላበት መሆኑን ተረድቷል፡፡  በመሆኑም ከድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ የተላከው የሊቀመንበሩ እገዳ ውሳኔ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ወስኗል፡፡
  2. በአቶ ዳውድ ፊርማ የተከናወነው እና የብሔራዊ ምክር ቤት ውሳኔ ነው ተብሎ ለቦርዱ የቀረበው የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እስከሚቀጥለው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሃላፊነታቸው ታግደው እንዲቆዩ  የተወሰነው ውሳኔ የስብሰባው በትክክል መካሄዱን የሚያሳይ ቃለጉባኤ የሌለው፣ ምን ያህል የምክር ቤት አባላት እንደተሳተፉበት እና በምን አይነት ድምጽ አሰጣጥ (አብላጫ ድምጽ የተወሰነ መሆን አለመሆኑን) መሆኑን የማያሳይ በሊቀመንበሩ ፊርማ ብቻ የተላከ ውሳኔ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት የፓርቲው ሊቀመንበርም ሆነ በሊቀመንበሩ ታግደዋል የተባሉት ስራ አስፈጻሚዎች ህጋዊ የድርጅቱ አካላት ሆነው ይቀጥላሉ፡፡ 

  1. ቦርዱ ከሁለቱም ወገኖች ጋር ባደረገው ውይይት ሁለቱም ወገኖች የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ በታህሳስ 2013 ዓ.ም መደረግ እንደሚገባው ምክር ቤቱ ቀደም ሲል የወሰነ እንደነበረ አረጋግጠዋል፡፡ በቦርዱ መስፈርትም መሰረት ኦነግ እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ ከሚገባቸው ፓርቲዎች አንዱ ነው፡፡ በተጨማሪም አሁን ባለው አለመግባባት የስራ አስፈጻሚ አባላቱ ሃላፊነታቸውን በመወጣት የአባላቶቻቸውን እና የፓርቲውን ጥቅም የሚያስጠብቁበት ሁኔታ ላይ እንዳልሆኑም በግልጽ ይታያል፡፡ በዚህም የተነሳ ለዚህ መፍትሄ ይሆን ዘንድ ሁለቱም ቡድኖች በጋራ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ ቦርዱ ወስኗል፡፡ ለዚህ ዝግጅት ሁለቱም ወገኖች የሚገኙበት የመጀመሪያ ስብሰባቸውንም በቦርዱ ስብሰባ አዳራሽ እንዲያከናውኑ  የተወሰነ ሲሆን ጊዜው ለሁለቱም አመራሮች የሚነገር ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ታህሳስ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top