Connect with us

የማይካድራ ተጠቂዎች አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል – ዶክተር ዳንኤል በቀለ ኢሰመኮ ኮሚሽነር

የማይካድራ ተጠቂዎች አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል - ዶክተር ዳንኤል በቀለ ኢሰመኮ ኮሚሽነር
Ethiopian press agency

ዜና

የማይካድራ ተጠቂዎች አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል – ዶክተር ዳንኤል በቀለ ኢሰመኮ ኮሚሽነር

የማይካድራ ተጠቂዎች አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል – ዶክተር ዳንኤል በቀለ ኢሰመኮ ኮሚሽነር

በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶክተር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል።

ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል፡፡

በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል። በመሆኑም ኢኮኖሚያቸው እንዲያንሰራራ እና ስነ ልቦናዊ ቀውስን መቋቋም እንዲችሉ ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ተጎጂዎቹ አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ የሚፈልጉ መሆናቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአካባቢው የሚገኙ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል

 የማይካድራ ጥቃት ቀላል የወንጀል ድርጊት አይደለም ፣ አስቀድሞ የታቀደ እና በጥንቃቄ የተቀናጀ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው ያሉት ዶክተር ዳንኤል፤ የአካባቢው የፀጥታ መዋቅር ለጥቃቱ ተጠያቂ ከሆነው ሳምሪ ከሚባለው ቡድን ጋር ተባብሮ ንጹሃንን ከጉዳት ከመጠበቅ ይልቅ ጥቃቱን መደገፉንና በጥቃቱ መሳተፉን አስረድተዋል፡፡

ወንጀሉ በአካባቢው በነበረው ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ድጋፍና ተሳትፎ የተፈጸመ ነው ያሉት ዶክተር ዳንኤል፤ ለወንጀለኞች ድጋፍ ያደረጉ እና የተሳተፉ የአካባቢው የፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በሕግ ፊት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል ፡፡

 ኮሚሽነሩ አክለውም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ተፈጽሞ የማይታወቅ አይነት ጭካኔ የተሞላበት የወንጀል ድርጊት እንዴት እንደተፈጸመና እንደተቀነባበረ ተጨማሪ ምርመራዎችን ማካሄድ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

የቅድሚያ ሪፖርቱ በቁጥር እና በጉዳት መጠን ላይ ትኩረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ዳንኤል፤ ጭፍጨፋው ያስከተለው የስነልቦና-ማህበራዊ ተፅእኖው እንዲሁም ወንድም ወንድም ላይ እንዴት እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ሊፈጽም እንደቻለ የዘርፉን ባለሙያዎች ትንታኔ እና አካታች ጥናት እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡(ኢፕድ)– 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top