Connect with us

“ ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ ” – የትህነግ የመቃብር ጽሑፍ !!

“ ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ ” - የትህነግ የመቃብር ጽሑፍ !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ ” – የትህነግ የመቃብር ጽሑፍ !!

“ ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ ” – የትህነግ የመቃብር ጽሑፍ !!

( ኃይሌ ተስፋዬ )

ኢትዮጵያ በታሪኳ ካስተናገደቻቸው አሳፋሪና ቅሌታም ገዥ መደቦች፥ የትህነግ ወያኔ ቡድን ግንባር ቀደሙን ይይዛል። ለዚህ ቡድን አምባገነን የሚለው ቃል ገላጭ አይደለም። ሽብርተኛ አሊያም ወንበዴ የሚለው ስምም ያንስበታል። ለህወሓት መገለጫ ስያሜ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው።

በዓለም ታሪክ ላይ እንዳነበብነው የአምባገነኖች የመጨረሻ እጣ ፈንታ በእግዜር ጣት ተገፍተው ከምድሪቱ መወገድ ነው። ለምሳሌ ያህል በቅዱስ መጽሐፍ ፦ ፈርኦንን፣ናምሩድን ፣ ናቡከደነፆርን እና ብልጣሶርን እንኳን ብንመለከት እነዚህ ሰዎች ሰዉነታቸው የሚታወቀው ልብስ በመልበሳቸው እንጅ፣ ከአውሬ የሚለዩ ግለሰቦች አልነበሩም።

ግብራቸውም እግዜርን የማይፈራ፣ ሰውንም የማያፍር ስለሆነ፣ የእግዜር ጣት በእነርሱ ላይ አርፏል። በእነርሱ ላይ ብቻም አይደለም፤ እንደነዚህ አይነት ግለሰቦች እና ቡድኖች ለምድሪቱም የርግማን ምክንያት ሊሆኑ ሁሉ ይችላሉ።

የትህነግ ባህሪም በዓለም ላይ ካየናቸው ክፉ ገዥዎች ቢበዛ እንጅ አያንስም። በጥቂቱ እንኳን ብንጠቅስ የትህነግ መንገድ፦ አረመኔነት፣ ክህደት፣ ማን አለብኝነትና አመጻ የተቀላቀለበት ክፉ ያሜኬላ መንገድ ነው። ከእግዜርም፣ከሰውም ጋር የሚጣል ግብረ ገብነት።

ይሁንና እነዚህ እንደ ግድግዳ ማንም የማይችላቸው የሚመስሉ ቋጥኞች ሲፈርሱ ጊዜ አይፈጅባቸውም። ምክንያቱም ልክ እንደ ብልጣሶር ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ ብሎ በአንድ ሌሊት ብን የሚያደርጋቸው፥ የራሔልን እንባ የሚመለከተው አፍራሹ አምላክ ስለሆነ ነው።

ትህነግ በሚዛን ተመዝና ቀልላ የተገኘች፣ መንግስቷም ለተመረጡት ተላልፎ የተሰጠ አምሳለ ብልጣሶር ናት ።

ሚዛኑም ህዝብ፣ መንግስቱም ህዝብ ነው !!

ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ ማለት ፦ በሚዛን ተመዘንህ፣ ቀለህም ተገኘህ፣ መንግስትህም ለሌላ ተላልፋ ተሰጠች ማለት ነውና።

ይህንንም መስፈርት ትህነግ ወያኔ በእጅጉ ታሟላለች !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top