Connect with us

አትክልት ተራ ከጃንሜዳ ሊነሳ ነው

አትክልት ተራ ከጃንሜዳ ሊነሳ ነው
አ/አ ፕረስ ሴክሬቴሪያት

ዜና

አትክልት ተራ ከጃንሜዳ ሊነሳ ነው

አትክልት ተራ ከጃንሜዳ ሊነሳ ነው

 

ከአትክልት ተራ ተነስተው በጃን ሜዳ እንዲሰሩ የተደረጉ የአትክልት ነጋዴዎች በቅርብ ቀን ወደ ተዘጋጀላቸው የገበያ ማዕከላት እንደሚዘዋወሩ የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ  እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን   በጀሞ ፣በኮልፌ ፣በሃይሌ ጋርመንት እና በሌሎች  አካባቢዎች በግንባታ ላይ ያሉ የአትክልት ገበያ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝታቸው በኃላ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት  ህዝብ መተፋፈግን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል ከአትክልት ተራ ተነስተዉ በጃን ሜዳ እንዲሰሩ የተደረጉ የአትክልት ነጋዴዎች በቅርብ ቀን ወደ ተዘጋጀላቸው የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉ ብለዋል።

የአዲስ የተገነቡና ነባር የገበያ ማዕከላት እድሳታቸው ተጠናቆ ቅድሚያ በጃን ሜዳ ላሉ የአትክልት ተራ ነጋዴዎች እንዲሰጡ ይደረጋል ያሉት ወ/ሮ አዳነች   ለስራ ክፍት ሲሆኑም ለአምራች ፣ ለነጋዴ እና ለሸማቹ የተሻለ የገበያ አቅረቦትና ትስስር እንደሚፈጥሩ አያጠራጥርም ሲሉ ገልጸዋል ።(አ/አ ፕረስ ሴክሬቴሪያት)

ተጨማሪ መረጃ፡- አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ ለምና እንዴት ተዛወረ?

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር የተወሰነው በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ነበር፡፡ ውሳኔው የተላለፈው የቀድሞ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ  ኢ/ር ታከለ ኡማ ከከተማው የፀጥታ አካላት ጋር አትክልት ተራ አካባቢ እየታየ ባለው መጨናነቅ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተገናኘ የሚኖረው አንደምታ ዙሪያ ከተወያዩ በኃላ ነው፡፡

ስለሆነም ከመጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የአትክልት ግብይቱ በጊዜያዊነት ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር ተወስኖ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

የአትክልት ግብይቱ ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር  የተደረገው ቦታው ሜዳማ እንደመሆኑ ለእንቅስቃሴ ምቹ መሆኑና ለቁጥጥር አመቺ መሆኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው ተብሎም ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በተግባር ሲታይ በቦታው ላይ ምንም ዓይነት መሰረተ ልማት አለመዘርጋቱና ለግብይትም አመቺ አለመሆኑ በተቃራኒው ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርግ የሚችል ሁኔታ በመፈጠሩ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሳ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top