Connect with us

የህወሓት ኢንዶውመንቶች እዳ ሲወራረድ

የህወሓት ኢንዶውመንቶች እዳ ሲወራረድ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የህወሓት ኢንዶውመንቶች እዳ ሲወራረድ

የህወሓት ኢንዶውመንቶች እዳ ሲወራረድ

 

(በፍቱን ታደሰ)

ሰሞኑን ህወሓት በባለቤትነት የሚያስተዳድራቸው 34 ግዙፍ የቢዝነስና የፋይናንስ ተቋማት የባንክ ሂሳባቸው ሙሉ በሙሉ መታገዱን ፌዴራል መንግስት አስታውቋል፡፡ ኤፈርት (ትዕምት/ ትካል ዕግሪ ምትካል ትግራይ) ተብሎ የሚታወቀው የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት ህወሓት በ17 አመት የትጥቅ ትግል ወቅት አገኘሁት ባለው ሃብት እንዳቋቋመው ይህንን ግዙፍ የኢንቨስትመንት ተቋም በኃላፊነት የመሩት አቶ ስብሃት ነጋና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ደጋግመው ይናገሩ ነበር፡፡

በሃገራችን በንግድና በኢንቨስትመንት የተሰማሩ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ፍትሃዊ የሆነ ነጻ የገበያ ውድድር እንዳይኖር የመንግሰትን ስልጣን በተቆጣጠረው ህወሓት ድጋፍ ጫና ያሳድራል በሚል ከፍተኛ ቅሬታ ቢቀርብበትም የሃገሪቱን መሪ ጨምሮ ሁሉም የኢህአዴግ አመራሮች ለኤፈርት አስፈላጊነት ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከሩ ነበር፡፡ የኤፈርት ድርጅቶች ሚሊዮኖችን ከባንክ ሲበደሩ ምንም አይነት ማስያዣ (Collateral) ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፤ ይባስ ብሎ ብድሩንም ሳይከፍሉ ይቀርና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ የተበላሸ ብድር ወይም በኪሳራ ምክንያት ሊመለስ የማይችል ብድር (bad debt) ተብሎ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡

ኢንዱስትሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሜካናይዝድ እርሻዎች፣ የማእድን ቁፋሮዎች፣ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋማት፣ ወዘተ. በኤፈርት ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሲሆን የእነዚህ ተቋማት ዋነኛ የፋይናንስ ምንጭ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጫና ከባንክ የሚገኝ ብድር ነው፡፡ ብድሩም በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ካቢኔ ውሳኔ የተበላሸ ብድር (bad debt) ተብሎ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ 

በኤፈርት ስር የሚገኙት ከዘጠና በላይ ፋብሪካዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የፋይናንስና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ ወዘተ. ሁሉም በሃያ አመታት ውስጥ ከመነሻ ካፒታላቸው እስከ 600 እጥፍ እድገት አሳይተው ቢሊየነር ቢሆኑም የተበደሩትን የባንክ ብድርም ሆነ የመንግስት ግብር አይከፍሉም፡፡ የተወሰኑትን ድርጅቶች የተነሱበትንና የደረሱበትን የካፒታል መጠን ስንመለከት፡- ጉና ኮርፖሬት በ10 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ተቋቁሞ አሁን ከ6ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያንቀሳቅሳል፣

መሶቦ ሲሚንቶ በ240 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ተቋቁሞ አሁን 9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያንቀሳቅሳል፣ ደደቢት ባንክ በ20 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ተመስርቶ አሁን 9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላይ ደርሷል፣ ብሩክ ኬሚካል በ20 ሚሊዮን ብር ተቋቁሞ አሁን ካፒታሉ 6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፣ ሱር ኮንስትራክሽን በ100 ሚሊዮን ብር ካፒታል ተመስርቶ ዛሬ 7 ቢሊዮን ብር ደርሷል፣ መስፍን ኢንጅነሪንግ ካፒታሉ ከ180 ሚሊዮን ወደ 10 ቢሊዮን አድጓል፡፡ ሁሉም የኤፈርት ድርጅቶች ከ40 እስከ 700 እጥፍ

ካፒታላቸውን አሳድገዋል፡፡

የኤፈርት ድርጅቶች ፍትሃዊ ያልሆነ የገበያ ውድድር እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል ከሚከሰሱበት ምክንያት አንዱና ዋነኛው በኢንትንዶውመንት ስም ተመዝግበው የመንግስት ግብር አለመክፈላቸው ሲሆን ከውጭ የሚያስገቡት ጥሬ እቃም ሆነ ተሸከርካሪ ያለቀረጥ መግባቱም በንግዱ አለም ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳርፏል፡፡ በአቶ ገብረየስ ቤኛ የሚመራውን አማልጋሜትድን ጨምሮ በርካታ ግዙፍ ድርጅቶችን ከስመው ከገበያ እንዲወጡ አድርጓል፡፡ በደፈናው ንብረትነቱ የትግራይ ህዝብ ነው ቢባልም ትክክለኛ ባለቤቱ ግን ማን እንደሆነ እንኳን የማይታወቀው ኤፈርት የህወኃት ቁንጮ አመራሮች ገቢውን እንደሚከፋፈሉት ይነገራል፡፡ 

ከባንክ የተበደረውን ለመክፈል ባለመቻሉ የሚቀርብበትን ወቀሳ ለማስተባበል ባለስልጣናቱ አትራፊ ድርጅት አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ለምሳሌ አቶ ስብሃት ነጋ በአንድ ወቅት ስለ ኤፈርት ሲናገሩ “ኤፈርት ሃገር ውስጥ አሉ ከሚባሉት ሃገራዊ ባለሃብቶች ወይም ኮርፖሬሽኖች በሃብት የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ ነው” ብለዋል፡፡ 

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም ኤፈርት ትልቅ ሃብት ያፈራና ለአገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን ደጋግመው ይናገሩ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ ብድሩን መክፈል አልቻለም እየተባለ ከህግ አግባብ ውጭ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የተበላሸ ብድር እየተባለ እንዲሰረዝለት ተደርጓል፡፡ የኤፈርት ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደሩት ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ አለመመለሱ ታውቋል፡፡

ሰሞኑን ከመንግስት በተሰጠው መግለጫ እንደታወቀው 34 የኤፈርት ድርጅቶች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ተደርጓል፡፡ ለኤፈርት ድርጅቶች በቢሊዮን አበድረው በወቅቱ ሃገር እየመሩ በነበሩ የህወሓት አመራሮች ተጽእኖ ገንዘባቸው ያልተመለሰላቸው ባንኮች ሂሳባቸውን የሚያወራርዱበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በብድር የወሰዱት ገንዘብ የህዝብ ገንዘብ በመሆኑ ሊመለስ ይገባል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤ ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  ነፃ ሃሳብ

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  By

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን...

 • የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  ነፃ ሃሳብ

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  By

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ ሰባት ቁጥርና ሕይወት፤ (አፈወርቅ ልሣኑ ~ ድሬቲዩብ) ሰባት ቁጥር...

 • ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release)

  ነፃ ሃሳብ

  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release)

  By

  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) “መንግስት የህግ...

 • ፖለቲከኞቻችን፣ዲያስፖራው፣ ሚዲያዎቻችን እና ማኀበረሰብ አንቂዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእሳት የሚፈተኑበት ወቅት ነው፤ እናስተውል ታሪክ ሰሪ እንጂ የታሪክ ተወቃሽ አንሁን ፖለቲከኞቻችን፣ዲያስፖራው፣ ሚዲያዎቻችን እና ማኀበረሰብ አንቂዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእሳት የሚፈተኑበት ወቅት ነው፤ እናስተውል ታሪክ ሰሪ እንጂ የታሪክ ተወቃሽ አንሁን

  ነፃ ሃሳብ

  ፖለቲከኞቻችን፣ዲያስፖራው፣ ሚዲያዎቻችን  እና ማኀበረሰብ አንቂዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእሳት የሚፈተኑበት ወቅት ነው፤

  By

  ፖለቲከኞቻችን፣ዲያስፖራው፣ ሚዲያዎቻችን  እና ማኀበረሰብ አንቂዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእሳት የሚፈተኑበት ወቅት ነው፤ እናስተውል ታሪክ ሰሪ...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top