Connect with us

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጣይዋ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተጠቃሚ አክሱም እንደምትሆን አምናለሁ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጣይዋ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተጠቃሚ አክሱም እንደምትሆን አምናለሁ፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጣይዋ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተጠቃሚ አክሱም እንደምትሆን አምናለሁ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጣይዋ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተጠቃሚ አክሱም እንደምትሆን አምናለሁ፡፡

አክሱም የስልጣኔ እንብርታችንነቷን ተባብረን አልምተን እውን እናደርገዋለን፡፡

(ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ)

የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ አክሱም አለ፡፡ አክሱም የቀደመ ስልጣኔያችን መነሻ ብቻ ሳትሆን የአብረሃም ልጆች እምነት የታሪክ ማዕከልና የዛሬ ማንነታችን ጭምር ምልክት ናት፡፡ አክሱም ለረዥም ዘመን ተተው ከተረሱ የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ መሆኗን ለመረዳት የአክሱምን ዙሪያ ገባ ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡

ፈጣሪ ግን እጆቹ ሰፊ ናቸው አክሱም ምድሯ ፍሬን ለመስጠት የተባረከ፤ ማጀቷ የማይጎድል፣ በረከቷ ለትውልድ የተረፈ ስፍራ ናት፡፡

በትግራይ የሚገኙ በርካታ ቅርሶች የመሰረተ ልማት፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እጥረትና የማስተዋወቅ ችግር አለባቸው፡፡ በእርግጥ እንዲህ ያለው ችግር የሁሉም የኢትዮጵያ መዳረሻዎች ችግር ነው፡፡

አክሱም ግን ከእኩዮቿ የቅርስ ከተሞች ጋር ስትነጻጸር አንዳች ያልተሰራባት መዳረሻ ናት፡፡አክሱም እኩዮቿ ቀደምቶቹ የዓለም መዲናዎች ናቸው፡፡

ዛሬ ከፒራሚዱ ያነሱ ጎብኚ ሊጎበኛት አይገባም ነበር፤ ዛሬ ከቻይናው ግንብ እኩል የነበረ ታሪክ ባለቤት መሆኗን የሚያሳይ ልማት የላትም፡፡ አክሱም የሰሜኑ ኢትዮጵያ የታሪካዊ የቱሪዝም ጉዞ መስመር እናት ብትሆንም ህዳር ካልሆነ መዲናዋ በጎብኚ የማይጨናነቅ መዳረሻ ናት፡፡

አምናለሁ ነገ ብሩህ ይሆናል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሩት ሀገርን በአንድ ልብ አነሳስቶ አንድን ስፍራ ድንቅ አድርጎ የማልማት ባህል ፊቱን ወደ አክሱም ያዞራል፡፡ ያኔ አክሱም ከቤተ ጊዮርጊስ እስከ አባ ጴንጤሌዮን ተራሮቿ ውብ ይሆናሉ፡፡ ታሪካዊ ይዘቱን ባልለቀቀ፣ መንፈሳዊ እሴቱን ባላጣ የዘመነ የቱሪዝም ልማት ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

ቀጣይዋ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተጠቃሚዋ መዲና አክሱም እንደምትሆን አልጠራጠርም፡፡ የስልጣኔያች እንብርት የሆነችውን መዲና ተረባርበን እውን እናደርገዋለን፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top