Connect with us

“ኦነግ ሸኔን እየጠራረግነው ነው” ~ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ኘረዝደንት

ኦነግ ሸኔን እየጠራረግነው ነው ~ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ኘረዝደንት

ዜና

“ኦነግ ሸኔን እየጠራረግነው ነው” ~ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ኘረዝደንት

ኦነግ ሸኔን እየጠራረግነው ነው ~ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ኘረዝደንት

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተላለፈ መልዕክት።

ህገ ወጡ የወያኔ ጁንታ ቡድን በኢትዮጵያ ብሄር ብሄርሰቦችና ህዝቦች ላይ ከፍተኛ በደል ሲፈጽም እንደነበር ሀገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ሀቅ ነው። በሀገራችን ለመስማት እንኳን የሚዘገንኑ ሰብዓዊ የመብት ጥሰቶችን፣ የተደራጀ የሀገር ሀብት ዝርፊያ፡ የዜጎች መፈናቀል፣አካል ማጉደል፣ አሰቃቂ ግድያዎችን መፈጸም፣ ባጠቃላይ አሰቃቂ ኢ-ሰብዓዊ የመብት ረገጣ መፈጸም የዚህ ሰው በላና ህገ ወጥ ጁንታ የሰርክ ተግባር እንደነበር ህዝባችን ከማንም በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ዘራፊው፣ከሃዳዊው የወያኔ ጁንታ ህዝቦች ላይ ሲፈጽመው የነበርው የበደል ጽዋ ሞልቶ በመፍሰሱ ህዝቡ በምሬት ከቤቱ ፣ከጫፍ እስከጫፍ ነቅሎ በመውጣት ይሄን ሰው በላ፣ ከሃዲና ዘራፊ ቡድን አንቅሮ በመትፋት ሲታገልው እንደነበር የሚታወቅ ጉዳይ ነው። በህዝቡ ግፊትና በለውጡ አመራር ሳቢነት በሀገራችን በተቀጣጠለውና በተፋፋመው የለውጥ እንቅስቃሴ የጁንታውን መረብ/ኔትወርክ በመበጣጠስ ህዝቡ የባርነት ቀንበሩን ከላዩ ላይ አሽንቀንጥሮ በመጣል ይህን ዘራፊ፣ገዳይና ከሃዲ ጁንታ ለአንዴና ለመጨረሻ ከላዩ በማስወገድ ጥግ እንዲይዝ አድርጓል።

ሆኖም ጁንታው ባለፉት ጊዜያት ሲፈጽማቸው የነበራቸውን በደሎች ለሀገር አንድነትና ሰላም፣ለወንድማማችነት መቻቻል፣ሲባል፡የለውጡ አመራር በሆደ ሰፊነት እና በትዕግስት በማየት/በማለፍ ባለፉት ጊዜያት የተፈጸሙትን እኩይ የቡዱኑ አስከፊና አሰቃቂ በደሎችን ሁሉ በመደመር ዕሳቤና በፍቅር እንዲታከሙ በሰፊው ጥረት ቢደረግም፡ይህን የመንግስትን ታጋሽነት ይህ ከሃዲ ቡድን እንደ ፍርሃት በመቁጠር የሀገር አንድነት ዓርማና የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች መመኪያና ጋሻ የሆነውን ጀግናው የመከለካያ ሰራዊታችን የሰሜን ዕዝ ላይ የፈሪ ዱላ በማሳረፍ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመፈጸም ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ከጀርባ ወግቷል።ይሄም በሀገራችን ጥቁር ጠባሳ የሆነ ትልቅ የክህደት ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ ከሃዲ፣ ዘራፊ ጁንታ ቡድን መላው ሀገራችን ወደ ትርምስ ለማስገባት እንድ ኦነግ ሸኔ አይነት ተላላኪና ቅጥረኛ የጥፋት ሀይሎችን መልምሎ በማሰለፍ፣የፋይናንስና የሎጄስቲክ ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያን በመውጋት ጸረ-ኢትዮጵያዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ፡ኢትዮጵያዊያንን በመግደል፣በመዝረፍ ሀገርን የሚያተራምስና የሚበጠበጥ የእኩይ ሴራ ባለቤት ቡድን ነው።

ሀገራችን ላይ በተፈጸመው ክህደት ህግን የማስከበር ግዳጅ/ዘመቻ ላይ የሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በሁለት ምዕራፎች ላስመዘገባቸው አንጸባራቂ ድሎች እና ለከፈለው፣እየኸፈለ ላለው አኹሪ መስዕዋትነት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ታላቅ ምስጋና እና አክብሮት ያለው መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ።ህዝባችን በመከላከያችን ላይ የተፈጸመው የክህደት ክህደት ድርጊት አስቆጥቶትና አስቆጭቶት በራሱ ተነሳሽነት ታላላቅ የከሃዲው ጁንታ የክህደት ድርጊት ውግዘትና የመከላካያችን የድጋፍ ሰልፎችን በማድረግ፣ ደም በመለገስ፣በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ የእርድ ሰንጋዎችና ፍየሎችን በማቅረብ፣እንዲሁም የገንዘብ መዋጮ በማድረግና እስከ ህይወት መስዕዋትነትም ከጎኑ በማሰለፍም ለጀግኖች ልጆች ያሳየው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እገልጻለው።

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ከሃዲውና ዘራፊው ጁንታ ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ እየወሰደ ባለበት በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ህዝባችንን የሚወጉ የወያኔ ትሮይ ተላላኪና ቅጥረኛ የኦነግ ሸኔ ላይ በኦሮሚያ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አነጸበራቂ ድሎችን በማስመዘገብ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ህግን የማስከበር ተልዕኮውን በድል አጠናቆ ወደ ቀድሞው መደበኛው ስራው እስኪመለስ ድረስ ህዝባችን እስከ ህይወት መስዕዋትነት ከጀግናው መከላከያችን ጎን ለመቆም የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል፡የኦነግ ሸኔን በመጠራረግ ህዝቦች፣በወንድማማችነት፡በዕኩልነት፡በፍቅርና በሰላም ሚኖሩባትን ኢትዮጵያና ኦሮሚያ ለማስቀጠል እንዲሁም እውን ለማድረግ የጀመርነው የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራችን የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጥላችኋለው።

ድል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን!
ድል ለኢትዮጵያዊያን!
ሽመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top