Connect with us

የአቶ ልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ

የአቶ ልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ
Photo: Social media

ዜና

የአቶ ልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ

የአቶ ልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ

 

አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት  ምስራቅ ችሎት ቀርበዋል። 

በችሎቱ ከአቶ ልደቱ ጋር አራቱ ጠበቆች ቀርበው በመሀል ዳኛው የፍርድ ቤት ብይን ፅሁፍ በንባብ ተሰምቷል። አጠቃላይ የብይኑ ጭብጥ በአማርኛ ተተርጉሞ ለአቶ ልደቱና ለችሎቱ ታዳሚዎች ተሰምቷል። 

ችሎቱ በአቃቢ ህግ የተጠቀሱት አንቀፅ 238 እና አንቀፅ 256 ግልፅነት የሚጎላቸው ናቸው። ስለዚህ አቃቢ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ተወስኗል። 

የዋስትና ጥያቄውንም ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እና ባልተሻሻለበት ሁኔታ ብይን መስጠት አንችልም በሚል ዋስትናውን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል።

አቶ ልደቱም ለችሎቱ ያላቸውን ሃሳብ አስረድተዋል። አቶ ልደቱ ከታሰርኩ አራት ወር ሆኖኛል። የእስከዛሬው የፍርድ ቤት ሂደት የሚያሳየው አቃቢ ህግ ዋና አላማው እኔን በወንጀል ከሶ የማስቀጣት ሳይሆን በተራዘመ የፍርድ ሂደት እኔን ማሰቃየት ነው።

የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል! 

የታሰርኩት በሴራ ነው!

ሴራውም እኔን በእስር ቤት በማቆየት አይምሮዬንና አካሌን አስሮ መቆየት ነው! 

ከዛም ሲያልፍ በህይወቴ ላይ አደጋ እንዲደርስ ማድረግ ነው!

ይሄ የተከበረው ፍርድ ቤት የዚህ እኩይ ስራ ተባባሪ መሆን የለበትም። ለችሎቱ እና ለለበሳችሁት ካባ ክብር ስትሉ ተገቢውን ፍርድ ትሰጣላችሁ ብዬ እጠብቃለሁ ብለዋል።

በመጨረሻም ችሎቱም የተሻሻለውን ክስ ለመስማት ለህዳር 24 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።(ምንጭ:- አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ሊቀመንበር)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top