Connect with us

የህወሓት አመራሮች አጣብቂኝ!!

የህወሓት አመራሮች አጣብቂኝ!!

ነፃ ሃሳብ

የህወሓት አመራሮች አጣብቂኝ!!

የህወሓት አመራሮች አጣብቂኝ!!

(ጫሊ በላይነህ)

መንግስት የመጨረሻ ዕድል ሰጥቷል ~ “በሰላም እጃችሁን ስጡ!!” ብሏል። ተሸናፊዎቹ በሰላም እጃቸውን ይሰጡ ይሆን ወይንስ እንደቴዎድሮስ ሽጉጣቸው ጠጥተው ያልፋሉ የሚለው  በጥቂት ቀናት ውስጥ ምላሽ ያገኛል።

ይኸ የፌደራል መንግስት “እጃችሁን ስጡ፤ ወገን አታስፈጁ!” የሚል ሀላፊነት የተሞላበት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የትኞቹን የህወሓት ባለሥልጣናትና ጋሻ ጃግሬዎቻቸውን ይመለከታል የሚለውን ከማስታወሳችን በፊት  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያወጣውን መግለጫ እናስቀድም።

የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሓት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ እና ተጨማሪ ግፍ ከመፈፀም እንዲታቀቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች እንደ ማይካድራ ባሉ ቦታዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

ይህ ቡድን  ባለፉት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የተቀናበሩ የወንጀል  ድርጊቶችን ሲፈፅም ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የፌዴራል መንግስት በእነዚህ የጥፋት ድርጊቶች ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

በትግራይ ክልል የተጀመረው  የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ  የተገለጸ ሲሆን፣ የህወሃት ቡድን   እንደ ማይካድራ ባሉ ቦታዎች ላይ የፈጸመው  ድርጊት በኢትዮጵያ ሕግም ሆነ በአለም አቀፍ ሕግ በወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ ጥፋቶች መሆናቸው ቡድኑ  ሊገነዘብ ይገባል ነው የተባለው።

የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው እና በዛሬው ዕለት በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ በመንግስት የተጠየቁት 64 የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉት ናቸው።

1.ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

2.ጌታቸው ረዳ

  1. ፈትለወርቅ ገ/እግዝያብሄር
  2. አስመላሽ ወ/ስላሴ

5.ዶ/ር አብርሃም ተከስተ

6.ኪሪያ ኢብራሂም

7.ረዳይ አለፎም

8.አማኑኤል አሰፋ

9.ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ

10.ኪሮስ ሀጎስ 

11.ያለም ፀጋ 

12.ሰብለ ካህሳያ

13.ጌታቸው አሰፋ

14.ዳንኤል አሰፋ

15.ኢሳያስ ታደሰ

16.ዶ/ር አክሊሉ ሀ/ሚካኤል 

17.አለም ገ/ዋህድ

18.ተክላይ ገ/መድህን

19.ዶ/ር እያሱ በርሄ 

20.ዶ/ር ረዳይ በርሄ 

21.ዶ/ር ኪዳነማርያም በርሄ 

22.ነጋ አሰፋ 

23.ሺሻይ መረሳ 

  1. ዶ/ር ገ/ህይወት ገ/እግዝያብሄር 
  2. አፅብሃ አረጋዊ 

26.ዶ/ር ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ

27.ሀዱሽ ዘነበ

28.በርሄ ገ/እየሱስ 

29.ይትባረክ አምሃ 

30.ዶ/ር ገ/መስቀል ካህሳይ 

31.ዶ/ር ፍስሃ ሀ/ፂዮን 

32.ርስቀ አለማየው 

33.ዶ/ር አዲስ አለም ቤሌማ 

34.ዘነበች ፍስሃ 

35.ፍሬወይኒ ገ/እግዝያብሄር 

36.አቶ ስዩም መስፍን 

37.አቶ አባይ ፀሐዬ

38.እያሱ ተስፋይ 

39.ለምለም ሀድጎ

 40.ፕሮፌሰር ክንድያ ገ/ህይወት 

41.ሀብቱ ኪሮስ 

42.በየነ ምክሩ

 43.ካሳዬ ገ/ህይወት 

44.ሩፈኤል ሽፈራ

 45.ሊያ ካሳ 

46.ተወለደ ገ/ፃዲቅ 

47.ሙሉ ገ/እግዝያብሄር 

48.ኪሮ ስጉዑሽ 

49.ዶ/ር አማኑኤል ሀይሌ 

50.ደሳለኝ ተፈራ 

51.ኢንጅነር አርአያ ብርሀኔ 

52.አልማዝ ገ/ፃድቅ 

53.ሰለሞን መአሾ 

54.ተኪኡ ማዕሾ

 55.ገነት አረፈ 

56.ብርክቲ ገ/መድህን 

57.ዶ/ር ሀጎስ ገዳፋይ 

58.ዘራይ አስጎዶም 

59.አሰፋ በላይ 

60.አቶ ሸዋንግዘው ገዛኸኝ 

61.አፅብሃ ግደይ 

62.አቶ ስብሀት ነጋ 

63.አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው

64.በሪሁን ተ/ብርሃን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ የነበሩ ናቸው፡፡

እነዚህ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮችና ጋሻ ጃግሬዎች የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው በአገር ክህደት ወንጀል፣ በከፍተኛ የአገር ሃብት ምዝበራና ዘረፋ እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀልም ጭምር የሚፈለጉ በመሆናቸው ነው ሲል የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አንድ የህግ ባለሙያ ለዚህ መጣጥፍ ዘጋቢ ስለጉዳዩ በሰጡት አስተያየት ህወሓቶች በሰላም እጃቸውን ከሰጡ ከምንም በላይ ታግለንለታል ሲሉት የነበረው ህዝብ ደህንነት እንዲረጋገጥ የሚረዳ ሲሆን በግልና በቡድን በሚቀርብባቸው ክስ  እንደአንድ የቅጣት ማቅለያ ቀርቦ ሊያዝላቸው የሚችልበት እድል አለ ብለዋል። በተቃራኒው በእምቢታቸው ከፀኑ በተገኙበት እርምጃ የሚወሰድባቸው ሲሆን የሚማረኩት ደግሞ ወደማይቀረው የፍርድ ችሎት ቀርበው ከፍተኛ ቅጣታቸውን ይቀበላሉ ብለዋል።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top