Connect with us

ኢትዮጵያ ደከመች ስትባል የምትጠነክር አገር ናት” 

ኢትዮጵያ ደከመች ስትባል የምትጠነክር አገር ናት”
Ethiopian News Agency

ዜና

ኢትዮጵያ ደከመች ስትባል የምትጠነክር አገር ናት” 

ኢትዮጵያ ደከመች ስትባል የምትጠነክር አገር ናት” 

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ኢትዮጵያ ደከመች ስትባል የምትጠነክር አገር ናት” ብለዋል።

በትግራይ የህወሃት ቡድንን ለህግ ለማቅረብና ህግ ለማስከበር በሚካሄደው ዘመቻ ህዝቡ ለአገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ የዚህ ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ወጣቱን በሰላም፣ በኢኮኖሚና በስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከሚፈጠረው የስራ ዕድል ወጣቱን 70 በመቶ ያህል ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ መቀመጡንም አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው ባደረጉት ገለጻ፤ በከተማዋ ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው።

በህወሃት ላይ እየተወሰደ ያለው ህግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top