Connect with us

የህወሓቶች ዕጣ ፈንታ፡- ከቀበሮ ጉድጓድ እንደአይጥ ተጎትቶ መውጣት ሊሆን ነውን?

የህወሓቶች ዕጣ ፈንታ፡- ከቀበሮ ጉድጓድ እንደአይጥ ተጎትቶ መውጣት ሊሆን ነውን?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የህወሓቶች ዕጣ ፈንታ፡- ከቀበሮ ጉድጓድ እንደአይጥ ተጎትቶ መውጣት ሊሆን ነውን?

የህወሓቶች ዕጣ ፈንታ፡- ከቀበሮ ጉድጓድ እንደአይጥ ተጎትቶ መውጣት ሊሆን ነውን?

(ጫሊ በላይነህ)

ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ዛሬ በትግራይ ኦንላይን ቲቪ አየሁት፡፡ ምስሉ ሳይ እንደሰው አዝኛለሁ፡፡ ምቾት ያጎሳቆለው ያ ፊቱ ጠቋቁሯል፡፡ ገጽታው ላይ ከፍተኛ ድካም ስሜት ይነበባል፡፡ ምናልባትም እንቅልፍ ከተኛ ቀናት አልፈውት ይሆናል፡፡ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ግን አሁንም የሚያወራው ስለአሸናፊነቱ ነው፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይነቱን ሊያስተጋባ ይሞክራል፡፡

 ሰውየው ነው አሉ፡፡ ተደባዳቢ ሚስት አለችው፡፡ አንድ የተረገመ ቀን ላዩ ላይ ሰፍራ በጥፊና በጡጫ ስታጣድፈው የሞት ሞቱን ኡኡታውን ያስነካዋል፡፡ ጎረቤት ተግተልትሎ ከች ይልና

“ምንድነው፣ ምን ሆናችሁ? ” ሲል፤ ባልየው ከስር ሆኖ የሞት ሞቱን

“ተጋደልን..ተጋደልን” አለ አሉ፡፡ ያው “ገደለችኝ” ማለቱ አሳፍሮት ነው፡፡

ዶ/ር ደብረጽዮንም ትላንት በጥጋብ ተኮፍሶ ስንቱን ሲዘላብድ ኖሯልና ዛሬ እንዴት ብሎ ስለሽንፈቱ ይናገር?..ካፈርኩኝ አይመልሰኝ ሆኖበት “ድል እያደረገ” መሆኑም ለመቀደድ አፉን ደንቀፍ እንኳን አላደረገውም፡፡

የሚገርመው መላው የትግራይ ሕዝብ እንዲዘምት እየተማጸና በሌላ በኩል ደግሞ በሁሉም ግንባሮች አሸንፈናል እያለ በራሱ ውሸት ራሱን ለማስደሰት መጋጋጡ ነው፡፡

ለዓመታት የፈጸመው ግፍ እና የበደል ጽዋ ሞልቶ መውጫ መግቢያ ባጣበት በዚህች ሰዓት ድረስልኝ የሚለው የትግራይ ሕዝብ ትላንትና ዞር ብሎ አይቶት አያውቅም፡፡ በ27 ዓመታት የስልጣን ዘመኑ ሌላው ሁሉ ቀርቶ ለዋና ከተማዋ መቀለ እንኳን የመጠጥ ውሃ ችግርዋን ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ ለመስራት ጊዜ አላገኘም፡፡ የትግራይ እናቶችን ጉስቁልናና ድካም የሚቀርፍ የፈየደው ነገር አልነበረም፡፡

ህወሓቶች በተለይ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ሙሉ በሙሉ ፊታቸውን ወደዘረፋና ውንብድና በማዞራቸው የትግራይን ሕዝብ የሚያስታውሱት በስሙ ሊነግዱ ሲፈልጉ ብቻ ነበር፡፡በስሙ መነገድ በፈለጉበት ሰዓት ሁሉ ያለሃፍረት ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው የሚል የተሰለቸ ነጠላ ዜማ እያቀነቅኑ ኖረዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ እና ህወሓት አንድ አለመሆናቸውን በጥቂቱ ለመገምገም በሰሞኑ የሠራዊታችን ህግን የማስከበር እርምጃ ከህወሓት ነጻ የሆኑ በርካታ አካባቢዎች የሕዝቡን ደስታ ብቻ መመልከት በቂ ነው፡፡ ሕዝቡ የተደሰተው እንደመዥገር ከተጣበቀበት የህወሓት አፋኝ ቡድን በመላቀቁ ነው፡፡ ገና ሠራዊቱ ከተማውን አጽድቶ ሳይጨርስ ሕዝቡ ፈንቅሎ ወጥቶ ደስታውን እየገለጸ ያለው በህወሓት እጅግ አድርጎ ስለተማረረ ነው፡፡

እናም ደብረጽዮን እና ጋሻ ጃግሬዎቹ  በዚህ በመከራ ወቅት የማያውቁትን የትግራይ ሕዝብን ምን አድርግ ይሉታል? እርግጥ ነው፤ በአሁን ሰዓት ህወሓት የቀድሞ ክብርዋን ተገፋለች፡፡ የተማመነችበት ልዩ ሃይላን ሚሊሽያዋ በቀላሉ ተበታትኖና እጅ ሰጥቶ እርቃናዋን አስቀርቷታል፡፡ አሁን በሠራዊትዋ የምትተማመንበት ጊዜ አይደለም፡፡

እናም የመጨረሻ ካርድዋ ከቻለች የትግራይን ሕዝብን ጎትታ ጦርነት ውስጥ በማስገባት የሠራዊቱ እርምጃ የዘር ማጥፋት ነው የሚል የሙት ካርድ ለመሳብ መቃብርዋ ላይ ቆማ ቋምጣለች፡፡ ግን ጭንቅ ላይ ናትና ለሁሉም ነገር መዘግየትዋ ሊገባት አይችልም፡፡ የትግራይ ሕዝም በሞት አፋፍ ላይ ያለ የወንበዴ ቡድንን ለማዳን ነፍሱን እንደማይገብርም የምትረዳው ሰሞኑን በምታየው ምላሽ ይሆናል፡፡  

አባቶች አማሟቴን አሳምርልኝ ይላሉ፡፡ ህወሓቶች መደምሰሳቸው ወይንም በሕይወት መያዛቸው ላይቀር  ሕዝብ ውስጥ መሽገው ከሚንፈራገጡ እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም ከተማ ውስጥ አልዋጋም ብለው እጃቸውን ቢሰጡ ለእነሱም ቢሆን የተሻለ አማራጭ በሆነ ነበር፡፡ ግን ይህ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ እናም በቀናት ውስጥ የተከበሩት የቀድሞ መሪዎቻችን ከቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ እየተለቀሙ የኣለም ማፈሪያና መሳቂያ የሚሆኑበት ቀን የማይቀር ዕጣ ፈንታቸው ይሆናል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top