Connect with us

ከህወሃት የጥፋት ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅር ይዘረጋል – ዶክተር ሙሉ ነጋ

ከህወሃት የጥፋት ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅር ይዘረጋል - ዶክተር ሙሉ ነጋ
Ethiopian News Agency

ዜና

ከህወሃት የጥፋት ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅር ይዘረጋል – ዶክተር ሙሉ ነጋ

ከህወሃት የጥፋት ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅር ይዘረጋል – ዶክተር ሙሉ ነጋ

ከህወሓት የጥፋት ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅት እንደሚዘረጋ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገለጹ።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመሰረት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወስኖ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ አስፈጻሚ በቅርቡ መሾሙና ደንብ መዘጋጀቱ ይታወቃል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዝርዝር ሥራዎችን በተመለከተ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሙሉ ነጋ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም “ጊዜያዊ አስተዳደሩ በዋናነት ሕገ መንግስትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያስከብራል” ብለዋል።

እስካሁን የጊዜያዊ አስተዳደሩ አጠቃላይ ሂደትን የሚያመለክት ቻርተር ተዘጋጅቶ መጠናቀቁንም ነው ዶክተር ሙሉ የገለጹት።

“የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የክልሉን ፕሬዚዳንት ሥራ የሚሰራ እንደመሆኑ መጠን አስፈጻሚ አካሉን ይመራል፤ ያስተባብራል” ሲሉም አክለዋል።

በዚሁ መሰረት ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዋቅር የማደራጀትና ሕዝቡን የማነቃቃት ሥራ እንደሚሰራ ነው ዶክተር ሙሉ ያመለከቱት።

ክልሉ ሙሉ በሙሉ ነጻ በሚወጣበት ጊዜም በክልሉ መንግስታዊ ሥራዎችን እንደሚያከናውን አመልክተዋል።

“የክልሉን ካቢኔ ያደራጃል፣ የዞን አስተዳደር ኃላፊዎችን ይሾማል” ያሉት ዶክተር ሙሉ፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ነጻና ገለልተኛ ምሁራን የሚሳተፉበት አስተዳደር የመመስረት ዓላማ እንዳለውም ተናግረው፤ “የትግራይ ሕዝብ ነጻነቱን እንዲጎናጸፍና በመረጠው አስተዳደር እንዲመራ ይደረጋል” ብለዋል።

ህወሓት ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ገደማ የልማት ሥራን አስቁሞ ‘ሕዝቡን ለክተት አዋጅ’ ሲያዘጋጅ እንደነበር ያስታወሱት ዶክተር ሙሉ፤ በክልሉ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ኢኮኖሚ የማነቃቃት ሥራ በትኩረት እንደሚከናወን ገልጸዋል።

ዶክተር ሙሉ አክለውም “የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የህወሓት ጁንታ በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን አስነዋሪ ተግባር ያወግዛል” ብለዋል።

ሥራ አስፈጻሚው መላው የትግራይና የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግስት የሕግ የማስከበር ሥራ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top