Connect with us

የገዱ አንዳርጋቸው ጥያቄ

የገዱ አንዳርጋቸው ጥያቄ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የገዱ አንዳርጋቸው ጥያቄ

የገዱ አንዳርጋቸው ጥያቄ

“ጥያቄዎች አሉኝ”

በህወሓት ቤት ሁሉም ነገር አልቆባቸዋል። ሃሳብ ካለቀባቸው ረዘም ያለ ጊዜ ሆነው። የቀሯቸው ጥቂት ታጣቂዎችና ዲጂታል ወያኔ ነበሩ። እነሱም በዚህ ሰሞን ተሰባበሩ። ታጣቂያቸው አክራሪዎቹ ያሉትን እና ዕድሜ ልካቸውን በውሸት እና በተስፋ በመገቡት የፕሮፓጋንዳ ስራ መታወር በፈጠረው ትእቢት ተጋርዶ የተዳፈነውን እሳት ነካክቶ እየተቃጠለ ነው። አንድን አባባል ዘንግቶ ይመስለኛል።

“ተው በሉት ያንን ሰው አይንካ ያንን ቤት፣

እሳቱ ቢጠፋ እረመጡ አለበት” የሚለውን

የዲጅታል ጦራቸው በሙሉ አቅሙ የብሔር ብሔረሰቡን ስም እየተጠቀመ አንዱን ከአንዱ ሊያፋጅ ያላደረገው ጥረት አልነበረም። የአቅሙን ሁሉ ሞክሯል። አልተሳካም እንጂ። አሁን ይህም ከነኔትወርኩ ድምጥማጡ ጠፍቷል።

እኔ አሁን ያሉኝ ጥያቄዎች የህወሓት መሪዎች በዚች ሰዓት በቡድን አስተሳሰብ/Group thinking/ እንደ ታሰሩ “ውድብና” እያሉ ወደ ሲኦል ሰተት ብለው ይገቡ ይሆን ወይስ ሲኦል በር ላይ ሲደርሱ እግዚአብሄር ለእያንዳንዱ ሰው የሰጠውን በግለሰብ ደረጃ የማሰብ ነፃነት ተገልጦላቸው ሁለት ነገሮችን ይናዘዛሉ? 

“በኢትዮጵያ ውስጥ በመንጋ የማሰብ፣ በመንጋ የማጥፋት፣ በመንጋ የመጮህ የእንስሳነት ባህሪ የተጠናወተው ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሄድንበት መንገድ መጨረሻው ጥፋት ነው” ብለው በግለሰቦች ነፃነት  ላይ የፈፀሙትን ወንጀልና በብሄር ብሄረሰብ የእኩልነት ጥያቄ ላይ የፈፀሙትን ሸፍጥ ተናግረው የሚቀረው እንዲማርበት ያደርጉ ይሆን?

ሌላስ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁና በታላቋ አገር ኢትዮጵያ የስልጣን ማማ ላይ ወጥተው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ከበረሐ ጀምሮ እንደልጆቹ አይቶ በንብረቱ፣ በጉልበቱና ከሁሉም በላይ መተኪያ የሌላትን ህይወቱን እየከፈለ ከልብ የደገፋቸውን የዋሁንና ሁሉ ዘመዴ የሆነውን የአማራ ህዝብ ወደ  ስልጣን ከወጡ በኋላ ከመሰሎቻቸው ጋር በመተባበር ለፍቶ አደሩን ያለ ስራው ወራሪ፣ ሰፋሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ ወዘተ በሚሉ ትርክቶች ሌሎች ወንድሞቹን አነሳስተው ያስከፈሉትን ፍዳ የሰሞኑን ጨምረው በፀፀት አንስተው ሌሎች ወገኖች እንዲማሩበት ኑዛዜ ያደርጉ ይሆን? 

በቃ ተፈፀመ!!

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top