Connect with us

ፍቅር ያሸንፋል ማህበር ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን ለማሳየት አገር አቀፍ የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጀ

ፍቅር ያሸንፋል ማህበር ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን ለማሳየት አገር አቀፍ የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጀ
Photo: በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

ፍቅር ያሸንፋል ማህበር ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን ለማሳየት አገር አቀፍ የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጀ

ፍቅር ያሸንፋል ማህበር ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን ለማሳየት አገር አቀፍ የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጀ

 (በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

አርቲስት ቻቺ ታደሰን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ያደረገው በማረሚያ ቤት ስቃይና በደል የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የመሰረቱት ፍቅር ያሸንፋል ማህበር በዛሬው ዕለት በዮድ አቢሲኒያ ሆቴል በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ላይ እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደሚደግፍና ድጋፉንም ለመግለጽ የደም ልገሳ መርሃግብር በመላ አገሪቱ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡

የፍቅር ያሸንፋል ማህበር መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚስባህ ከድር እና ሌሎች የማህበሩ አመራር አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የማህበሩ አባላት በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ብዙ ግፍና በደል ከደረሰባቸው ወገኖች መካከል መሆናቸውን ነገርግን ግፉን ረስተው ሳይሆን ይቅር ብለው ማህበሩን መስርተው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ቀደም ሲል ችግሮችን አስቀድሞ ለመፍታት እንዲቻል ጉዳዩን በእርቀሰላም ለመፍታት የህወሓት አመራሮችን ጭምር በተደጋጋሚ በመጋበዝ ማህበሩ ብዙ ጥረቶችን ቢያደርግም ፍቃደኛ ሆነው ሊገኙ ባለመቻላቸው አለመሳካቱን ተናግረዋል፡፡ ችግሮች በጠረጼዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ብሔራዊ መግባባት እንዲመጣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖች አባቶች ጋር በመሆን ለአገር ሰላም ማህበሩ አቅም የፈቀደውን አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱን አቶ ሚስባህ አስታውሰዋል፡፡

ህወሓት ከ20 ዓመት በላይ ድንበር ሲጠብቅ ከኖረው መከላከያ ሰራዊት ላይ ያካሄደው ኢሰብኣዊ ጥቃት አጥብቀው እንደሚያወግዙት የገለጹት የፍቅር ያሸንፋል ማህበር አመራሮች መከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ህዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስአበባ፣ በአዳማ፣ በባህርዳር እና በሌሎችም ክልሎች የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ደም የመስጠት ፕሮግራም እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

የማህበሩ አባል ሳሮን ሐጎስ በሰጡት አስተያየት ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነው እያሉ ለዘመናት በስማችን ነግደዋል፡፡ የህወሓትን ግፍ መንግስት በቃ ማለት አለበት፡፡ የተጀመረው ሕግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የትግራይ ሕዝብ የለውጡ ተቋዳሽ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

አርቲስት ቻቺ ታደሰ የማህበሩ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ለድሬቲዩብ በሰጡት ቃል ህወሓት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የፈጸመው ጥቃት እንዳሳዘናት ገልጻ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም አስፈላጊውን የዜግነት ግዴታ ለመወጣት መዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡ የማህበሩ ዓላማ እንዲሳካ የበኩሏን ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ጠቅሳ ባለፈው ዓመት በኮቪድ 19 ችግ ምክንያት በመተላለፉ እንጂ “ለፍቅር እንሩጥ፣ ጥላቻን እናምልጥ” በሚል መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የአምስት ኪሎ ሜትር  የሩጫ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ከ20 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ለመሳተፍ ተመዝግበው እንደነበር አስታውሳለች፡፡

ፍቅር ያሸንፋል ማህበር አባላት በዘመነ ሕወሓት በአመለካከትና በብሔራቸው ምክያት ያለስራቸው ስራ፣ ያለስማቸው ስም ተሰጥቷቸው፣ በሽብርና በሌሎችም የሀሰት ወንጀሎች ተከሰው በማረሚያ ቤት ከፍተኛ ስቃይና ግፍ የተፈጸመባቸው ዜጎች በደላቸውን በይቅርታ በመሻር ማህበሩን ማቋቋማቸው የሚታወስ ነው፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top