Connect with us

የፈንቅል ጥሪ – ለትግራይ ወጣት

የፈንቅል ጥሪ - ለትግራይ ወጣት
Photo: Social media

ዜና

የፈንቅል ጥሪ – ለትግራይ ወጣት

የፈንቅል ጥሪ – ለትግራይ ወጣት

የትግራይ ወጣት ህገወጡን የህወሓት ከሀዲ ቡድን ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደ ዕድል ተጠቅሞ ከቡድኑ ቅኝ አገዛዝ ራሱን እንዲያላቅቅ ፈንቅል ጥሪ አቀረበ።

የፈንቅል የጋራ አመራር አስተባባሪ ወጣት ሚኪ ተስፋዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቀው፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን በመላው የትግራይ ህዝብ ስም ሲነግድና የአገሩ ልማት ባይተዋር አድርጎት ለዓመታት በጭቆና ቀንበር ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል።

 በተለይም ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ትግራይ ውስጥ በመመሸግ ወጣቱን በማሳደድና ወደማይፈልገው የጦርነት አውድ እንዲሰለፍ በማድረግ ከፍተኛ ጫና ሲያደርስበት ቆይቷል። በመሆኑም ወጣቱ ራሱንም ሆነ መላውን የክልሉን ህዝብ ከቡድኑ ጨቋኝ አገዛዝ ለማላቀቅ አሁን እየተደረገ ያለውን ህገወጡን ቡድን የማስወገድ ዘመቻ ሊደግፍ ይገባል።

ፈንቅል ከምስረታውም ጀምሮ ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሃይል እርምጃ ብቻ መወገድ አለበት ብሎ እንደሚያምን ያስታወሰው ወጣት ሚኪ ፣ አባላቱ ራሳቸውን ከዲሞክራሲያዊ ትግል በማግለል አመፅ በማነሳሳት ህዝቡ የከሀዲውን የህወሓት ቡድን ጨቋኝ አመራር አሻፈረኝ እንዲል ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አመልክተዋል።

ቡድኑ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የእኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክል የሚል ፅንፍ የረገጠ አቋም ያለው፣ ይህንን አቋሙን እስከዛሬ ያልቀየረ፣ በዚህ አቋም ከመጣህበት ስለሀገርም ሆነ ስለህዝብ ደንታ የሌለው መሆኑን አመልክቷል። 

በአሁኑ ወቅትም ስልጣኑን ለማስቀጠልና ከተጠያቂነት ለማምለጥ የትግራይ ህዝብ ምሽግ ማድረጉን አስታውቋል።

 በሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ በመንዛትና የፌዴራሉ መንግስት ላይ ጥላቻ በመዝራት ህዝቡ ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ተለይቶ እንዲኖር አፍራሽ ስራ ሲያከናውን መቆየቱን አብራርቶ ፣ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝቡን ሃብት በመጠቀም ወጣቱን በገንዘብ በመደለል ያለፍላጎቱ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ገልጿል።

ይህ ህገወጥ ቡድን ማህበረሰቡን እያደኸየ ሲገዛበት የነበረው መንገድ መጨረሻ ላይ አደጋ ውስጥ እንደጣለው አመልክቶ ፣ ትግራይ ውስጥ ገብቶ ከመሸገ በኋላ የህዝብ ገንዘብ እየተጠቀመ በተላላኪዎች አማካኝነት አገሪቱን የመበጥበጥ ስራ ላይ መጠመዱን አስታውቋል።

የገንዘብ ለውጡን ተከትሎ አቅሙ እየታደከመ በመሄዱ ያደርገው የነበረው እንቅስቃሴ ተገትቷል ፤በዚህም የተነሳ የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ የተጠቀመው ህዝብ ሲጠብቅ በኖረ የአገር መከላከያ ላይ ጥቃት መሰንዘር መሆኑን ገልጿል።(ኢፕድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top