Connect with us

ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዐረፉ

ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዐረፉ
Photo: ሐራ ተዋሕዶ

ዜና

ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዐረፉ

ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዐረፉ

 

  • የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው ነገ ጠዋት በ3፡00 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

የቀድሞው የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ዛሬ ጠዋት ዐርፈዋል፡፡

ከሓላፊነታቸው ተገልለው በመንበረ ፓትርያርኩ በሚገኘው ማረፊያቸው ለረጅም ጊዜ በሥጋ ሕመም የቆዩት ብፁዕነታቸው፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም.  ጠዋት በሞተ ሥጋ ተለይተውናል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ በአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ፣ ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም. ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙት 16 ብፁዓን አባቶች አንዱ ነበሩ፡፡ በፊት ስማቸው አባ አምኃ ሥላሴ ይባሉ የነበሩ ሲኾን፣ ብፁዕ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው ለከፋ ሸካ ሀገረ ስብከት ተመድበው ነበር ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን የጀመሩት፡፡

የብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የቀብር ሥነ ሥርዐት፣ ነገ ኀሙስ፣ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00፣ በመንበረ  ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች እና የድርጅቶቹ ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት ሓላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

(ሐራ ተዋሕዶ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top