Connect with us

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረስ  ከገደብ ያለፈ ጥፋት ነው፦ሽመልስ አብዲሳ

የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን በሚሰራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረስ ከገደብ ያለፈ ጥፋት ነው፦ሽመልስ አብዲሳ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረስ  ከገደብ ያለፈ ጥፋት ነው፦ሽመልስ አብዲሳ

የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን በሚሰራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረስ  ከገደብ ያለፈ ጥፋት ነው፦ሽመልስ አብዲሳ

የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን በሚሰሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረስ  ከገደብ ያለፈ ጥፋት ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ለሀገሪቱ ሰላም ዘብ የቆመውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ  ዛሬ ጥቃት ያደረሰው የህወሓት የጥፋት ሃይል ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ገልጸዋል።

የህወሓት የጥፋት ቡድን በሀገሪቱ ዜጎች ላይ በህገወጥ የታጠቁ ሃይሎችን በቁሳቁስና በገንዘብ  በመደገፍ የሀገርን ሰላም እያወከ እንደነበር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።

ቡድኑ በትግራይ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱንና ይህ ቡድን ኦነግ ሸኔን በማስታጠቅና በመደገፍ የጥፋት ተግባሩን እየፈጸመ ነው ብለዋል።

ህወሓት በአሁኑ ወቅት ተስፋ በመቁረጥ የመጨረሻ አማራጩን እየተጠቀመ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ለጥፋት ያሰለጠናቸውን ሃይል በመጠቀም  ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ሲያደርስ እንደነበረ ማስታወሳቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።(EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top