Connect with us

በጀርመን ኮሮና በማገርሸቱ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተገደደች

በጀርመን ኮሮና በማገርሸቱ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተገደደች
Photo: Social media

ዜና

በጀርመን ኮሮና በማገርሸቱ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተገደደች

በጀርመን ኮሮና በማገርሸቱ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተገደደች

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

በጀርመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማገርሸቱ ላልቶ የነበረው ሕግ እንደገና በማጥበቅ በሬስቶራንቶች፣ የሰውነት ማጎልመሻ ስፖርት ስፍራዎች እና ቲያትር ቤቶች ለወራት የሚቆይ ክልከላን ይፋ አደረገች፡፡ ይህን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው በዋናነት የኮሮና ቫይረስ በሆስፒታሎች ውስጥ ከመጠን በላይ ጫና እየፈጠረ በመምጣቱ እንደሆነ ቻንስለር አንጄላ ሜርክል ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ቻንስለር አንጄላ ሜርክል እንዳሉት «እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ወረርሽኙ እየተስፋፋ እና እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ወረርሽኙን ለማፈን በጠንካራ ሁኔታ በመስራትእና የህዝቦች ግንኙነትን በመቀነስ ወረሽኙን ማስቆም ይቻላል፡፡” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

እ.ኤአ. ከኖቬምበር 2 ጀምሮ በሬስቶራንት ፣በባር፣በትያትር ቤት፣ሲኒማ፣ፑል ቤትና ጂም ቤት ውስጥ ቢበዛ ከ10 ሰው በላይ ማስተናገድ ከመከልከሉም በላይ የተያዙ ኮንሰርቶች ጭምር  እንዲሰረዙ ሆኗል፡፡

ክልከላው በተጨማሪም በመደበኛነት የሚካሄደውን የስፖርት ዝግጅቶች ያለምንም  ደጋፊ መካሄዳቸው ይቀጥላል፡፡ በተጨማሪም ከስራ ጋር ባልተያያዘ ጉዳይ እና አላስፈላጊ በሆኑ ምክንያቶች ጉዞ ማድረግ አይቻልም፡፡ እንዲሁም ሆቴል ይዞ ማረፍም ቢሆንም በጣም አስፈላጊ ለሆነ የቢዝነስ ጉብኝቶች ብቻ ተፈቅዷል፡፡

ይህንንም አስከትሎ የድሆንጋ ሆቴል እናሬስቶራንት ማህበር ይህን ውሳኔ «መራራ ነው» ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ብዙ የንግድ ስራዎች ግርግዳችን በጀርባቸው ተደግፈው ቆመዋል፡፡ ተስፋ መቁረጣችን እየጨመረ ነው ሲሉ የድሆጋ ቼፍ ኤክስኪቲቭ ኢንግሪድ ሀርነትስ ገልፀዋል፡፡

አዲስ በወጣው አዋጅ መሰረት ት/ቤቶች እና የህፃናት ማቆያ እንዲሁም ሱቆች ክፍት እንዲሆኑ፤በተያያዘም ርቀታቸውን እንዲጠብቁና የንፅህናአጠባበቅ ደንቦችን እንዲፈፀሙ በጥብቅ ኣሳውቀዋል፡፡

በሀገርአቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የክልላዊ እርምጃዎችን ግራ የሚያጋባ ሂደቶች ይተካሉ፡፡

ይህንን አዋጅ ለማጣጣም ጀርመን በአዲሱ ገደብ ሳብያ የተጎዱትን በተለይም ለአነስተኛ ኩባንያዎች  የገንዘብ ድጋፍ እንደምታደርግ ኣሳውቃለች፡፡በመሆኑም 10 ቢሊዮን ዩሮ ለ50 ኩባንያዎች 75 በመቶ  የሚሆን የአመት ገቢያቸውን ሸፍኖላቸዋል፡፡

በተጨማሪም በግል ለሚሰሩ ሰራተኞች ደግሞ ለአርቲስቶች እና የመድረክ ሰራተኞች አስቸኳይ የሆነ ብድሮች እንዲያገኙ የሀላፊነት መርሀ ግብሩን በማስፋት አነስተኛ ይዘት ላላቸው ከ10 በታች ሰራተኞች ደግሞ በጣም አነስተኛ ብድር መንግስት እንደሚሰጥ ተገልጻል፡፡

ከአውሮፓ በትልቅ ኢኮኖሚ ጀርመን ተጠቃሽ ስትሆን በስፋት ወረርሽኙ እየተስፋፋባት እና የሞት ቁጥርም ከሌሎች የጎረቤት ሀገራት በላይ እያስመዘገበች በመሆኗ ከመጀመሪያዎች ማሃከል እንድትገኝ አድርጓታል፡፡

ባለፈው ሳምንት በ24 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ወረርሽኙ ከ14 ሺ 964 ተነስቶ ወደ 464 ሺ 239  መድረሱን የጀርመን የተላላፊ በሽታ ወኪል ኢንስቲትዩት ሮበርት ኮች  አስታውቀዋል፡፡

የሞቱት ብዛት ከ85 ወደ 10 ሺ 183 ያደገ ሰሆን በቀጣይ ይህ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እና ሊስፋፋ እንደሚችል በማሰብ ስጋት ውስጥ እንደሚከት ሜርክል ባቀረቡት ማስጠንቀቂያ ገልፀዋል፡፡

«የጤና ስርአታችን ለመቋቋም አሁንም እየታገልን እንገኛለን፤ ግን በዚህ ሳምንት እንኳን ወረርሽኙ በፍጥነት በመባዛት ላይ ነው» ሲሉ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

ቻንስለር ሜርክል በተጨማሪም እንደገለፁት ከዚህ በኋላ ወረርሽኙን 75 በመቶ ዙሪያ ያለውን  በመቆጣጠር ውጤታማ መሆን ይቻላል ብሎ ለማሰብ አስቸጋሪ እንደሚሆን አክለዋል፡፡

ለአራት ሳምንታት ይህን ካደረግን በፍጥነት መጨመሩን ሊያቆም እና በድጋሚ ደህንነት ሊሰማን ይችላል ብለዋል፤ ቤርሊን ማየር ማይክል ሙለር ፡፡

ሜርክል እና ሌሎች 16 የጀርመን ክልል መሪዎች በከፊል የመዝጋቱን  ጉዳዩ  በዚህ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደገና ተገናኝተው ውጤታማነት እንዳለው ለመገምገም ተስማምተዋል፡፡ (ምንጭ፡- ሮይተርስ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top