Connect with us

የንግድ ባንክ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” የሎተሪ ዕጣ ወጣ

የንግድ ባንክ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” የሎተሪ ዕጣ ወጣ
Commercial Bank of Ethiopia

ዜና

የንግድ ባንክ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” የሎተሪ ዕጣ ወጣ

የንግድ ባንክ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” የሎተሪ ዕጣ ወጣ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላለፉት 9 ወራት ሲያካሂደው የነበረው የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” የቆጣቢዎች የሽልማት መርሀ-ግብር ዕጣ በብሔራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በይፋ ወጥቷል፡፡ 

የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የባንኩ አመራሮች፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሀላፊዎች እና ተወካዮች፣ ደንበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በወጣው ዕጣ ከታህሳስ 23 ቀን 2012 እስከ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከብር 500 ጀምሮ በመቆጠብ የእድል ኩፖን ቁጥር ያገኙ ደንበኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባደረጉት ንግግር፣  የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” የቆጣቢዎች የሽልማት መርሀ-ግብር በርካቶች ወደ ባንክ አገልግሎት እንዲሳቡና የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡

ሀብት በማሰባሰብ የሀገራችንን ልማት ከመደገፍ አንፃር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ትልቅ ሀላፊነት እንደተጣለ የገለጹት አቶ አቤ፣ ይህን በብቃት ለመወጣት ባንኩ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መጋቢት 2004 ዓ.ም የተጀመረው የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ-ግብር በሀብት ማሰባሰብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ አቶ አቤ አክለው ገልፀዋል፡፡ 

ለ9 ዙሮች በተካሄደው የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!”  መርሀ-ግብር መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ደንበኞቻችንን የታላላቅ ሽልማቶች እድለኛ አድርጓል፡፡ 

በታዛቢዎች ፊት በወጣው 9ኛው ዙር የሽልማት መርሀ-ግብር ዕጣ 2 ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርታማዎች፣ 3 መለስተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ 15 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች እና 30 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች በአጠቃላይ 50 ሽልማቶች ለእድለኞች ደርሰዋል፡፡

በዚህ መሠረት፡

  • በ1ኛ እጣ 2  አፓርታማ ቤቶች የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች 0000311398898 እና 0382600157224፤ እንዲሁም
  • በ2ኛ ዕጣ 3 መለስተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች 0034700387640 ፣ 0000762333420 እና 0167600256722 በመሆን ወጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቆጣቢ እድለኞቹ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!!!

ማስታወሻ:-  15 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች እና 30 ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የሚያስገኙትን የዕጣ ቁጥሮች ዝርዝር በቀጣይ እንደሚገለፅ ባንኩ አስታውቋል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top