Connect with us

“እናመሰግናለን!”

"እናመሰግናለን!"
የአ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት

ማህበራዊ

“እናመሰግናለን!”

“እናመሰግናለን!”

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  በቅርቡ  አስራ አንደኛ ክፍለ ከተማ በአዲስ እንዲዋቀር የወሰነው  ውሳኔ በአካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ጥያቄ በመመለስ  የአገልግሎት አሰጣጡን  ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የሚረዳ ነው ተባለ፡፡

ለሚ ኩራ የአዲስ አበባ 11ኛው ክፍለ ከተማ ሆኖ መዋቀሩን በማስመልከት  የአካባቢው ነዋሪዎች ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በቅርቡ  ባካሄደው 8ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ለሚ ኩራ በሚል  አስራ አንደኛ ክፍለ ከተማ እንዲዋቀር ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው።

የከተማ አስተዳደሩን ውሳኔ በማስመልከት   በየካ  እና በቦሌ ክፍለ ከተሞች ስር በመሆን ይተዳደሩ የነበሩት የሰሚት፣ የመሪ፣ የአያት ፣የካ አባዶ ጎሮ : አይሲቲ ፖርክ እና  አካባቢ ነዋሪዎች በአያት አደባባይ በመገኘት ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል::

ክፍለ ከተማው በአቅርቢያችን መዋቀሩ አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በቅርበት ለማግኘት እና እንግልትን ለመቀነስ፤ ለልማት መፋጠን እና መልካም አስተዳደር ችግሮች መፈታት ሁለንተናዊ   ፋይዳ  ይኖረዋል ያሉት ነዋሪዎቹ የለውጡ አመራር  ለዘመናት የቆየውን የህዝብ  ጥያቄ  በአፋጣኝ መልስ በመስጠቱ መደሰታቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ 

ውሳኔው ተገቢ እና ወቅታዊ  መሆኑን  የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች  በአዲሱ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ጉዳናዎች የጽዳት ዘመቻ ዘመቻና የእግር ጉዞ አካሂደዋል፡፡

በምስጋና መርሃ-ግብሩ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌ  እና የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን አምባዬ  እንዲሁም የአዲሱ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ  ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ መሀመድ በእንግድነት ተጋብዘው  ለአካባቢው ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል::(የአ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

 

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top