Connect with us

ዛሬም በጉራፈርዳ…

ዛሬም በጉራፈርዳ...
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ዛሬም በጉራፈርዳ…

ዛሬም በጉራፈርዳ…

(ገዱ አንዳርጋቸው)

የአማራ ህዝብ ለፍትህ፣ለነፃነት እና ለአብሮነት ሲታገል  ቢኖርም እስካሁን በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም፣ፍትህና የህግ የበላይነት ሰፍኖ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በሰላም ፣ በነፃነት እና በደስታ መኖር የሚቻልባት አገር ባለቤት መሆን አልተቻለም።

ይልቁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግፍና መከራው አየተጠናከረ በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋና በገፍ መፈናቀሉ ተስፋፍቶ ቀጥሏል።ይህንን ሁኔታ ለመረዳት ብዙም ሩቅ ሳንሄድ ይህንን አንድ አመት ብቻ ወስዶ አዝማሚያውን መገምገሙ ብቻ በቂ ነው። 

ከጥቅምት እስከ ጥቅምት ያለው አንድ አመት ብቻ  በግልፅ የሚነግረን ግፍና መከራው ተጠክሮ መቀጠሉን ነው። ማለቂያ የሌለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣በገፍ መፈናቀል፣የዘመናት የልፋት ውጤት የሆነ ንብረት ውድመት የየሳምንቱ መርዶ መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል።

ስለሆነም ነገሩን ላለማባባስ ሲባል በዝምታ ማለፋ የሚጎዳ መሆኑን በተግባር እያየነው በመሆኑ ያገባናል ባዮች በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል።ይህ በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው በማንም ህዝብ ሳይሆን በጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች ሴራ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ በአጋርነት የሚያሰልፍ የትግል አቅጣጫ ነድፎና  ስትራቴጅያዊ ግብ ወስኖ በጋራ መንቀሳቀስ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም። 

በክስተት ላይ ያነጣጠረ ጩኸት አልቃሻ ከማድረግ የዘለለ ጥቅም የለውምና።(ከፌቡ ገፃቸው የተወሰደ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top