Connect with us

ባለስልጣኑ በሕገወጥ የምግብና መድሃኒት ምርቶች ላይ እርምጃ ወሰደ

ባለስልጣኑ በሕገወጥ የምግብና መድሃኒት ምርቶች ላይ እርምጃ ወሰደ
ፎቶግራፍ:- አቶ አበራ ደነቀ፣ አቶጌታቸው ገነቴ፣ አቶ በትረ ጌታሁን

ህግና ስርዓት

ባለስልጣኑ በሕገወጥ የምግብና መድሃኒት ምርቶች ላይ እርምጃ ወሰደ

ባለስልጣኑ በሕገወጥ የምግብና መድሃኒት ምርቶች ላይ እርምጃ ወሰደ

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

የኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት ባለስልጣን በ2013 የበጀት ዓመት የመጀመሪያው ሶስት ወራት የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ 24.2802 ቶን የተለያዩ የምግብ ሸቀጦች ወደአገር ውስጥ እንዳይገቡ ማድረጉን አቶ አበራ ደነቀ የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡

ባለስልጣኑ በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተሰሩ የቁጥጥር ስራዎችና የተወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ  ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ባለስልጣኑ በምግብ ዘርፍ ባደረገው ቁጥጥር ከታዩ ግድፈቶች መካከል የአስገዳጅ ደረጃ አለመሟላት፣ የአጠቃቀም መመሪያ አለመለጠፍ፣ የምርቱ መጠቀሚያ ጊዜ ለማወቅ የአሰራር ስርዓት አለመኖር፣ የተበላሹ የምግብ ምርቶች ማቆያ ቦታ አለመዘጋጀት፣ የጥሬ ግብዐት አቀማመጥ ስርዓት አለመጠበቅ እና የአሰራር ስርዓት አለመዘርጋት መታየታቸውን አቶ አበራ አስረድተዋል፡፡

ስጋትን መሰረት ባደረገ የምግብ ምርቶች ላይ ናሙና በመውሰድ የላብራቶሪ ምርመራዎች የተሰሩ ሲሆን በዚህም ሒደት ከተመረመሩ የጁስ ምርቶች፣ የጨቅላ ህጻናት ወተት፣ የዘይት ናሙናዎች፣ የዱቄት ወተቶች፣ ብስኩቶችና ሌሎች ምርቶች በጠቅላላው 247 ናሙና መውሰድ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ ቁጥጥር ወቅት 21 አምራቾችና አስመጪዎች የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንደአቶ አበራ ገለጻ በገበያ ውስጥ የህገወጥ ምርቶች ዝውውር እንዲቀንስ ከማድረግ አንጻር ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀሉ እና ሕገወጥ የምግብ ምርቶችን የመለየት፣ የመከላከል እና ምላሽ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡ ከባዕድ ነገር ጋር እንደተቀላቀሉ የተደረሰባቸው እንደዘይት፣ ጨው፣ የለውዝ ቅቤ፣ ቪምቶ፣ አቼቶ፣ ከረሜላ፣ማር፣ ሞሪንጋ  እና የመሳሰሉ ምርቶች በ14 ከተሞች ተገኝተው እንዲታገዱ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ ባለፉት ሶስት ወራት 13 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የእጅ ጓንት፣ ከግል ፍጆታ በላይ የመጣ ማስክና ያልተፈቀዱ የግንባር ሙቀት መለኪያዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ወደአገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

ባሳለፍነው ሩብ ዓመት በኢንስፔክሽን ግኝቶችና የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶች መሰረት በማድረግ በ23 የመድሃኒት ተቋማትና የመድሃኒት ሕክምና መሳሪያዎች ጅምላ አከፋፋዮች፣ ሳኒታይዘር አምራቾች፣ የኮስሞቲክስ አስመጪ ተቋማት፣ የፍቃድ ስረዛ፣ እገዳ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እና የማስተካከያ የጽሑፍ ግብረ መልስ የመስጠት እርምጃዎች በባለስልጣኑ በኩል መወሰዱን አቶ አበራ ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም በአዲስአበባና ዙሪያዋ የሚገኙ መ/ቤቶች የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ናሙና በመውሰድ 10 ተቋማት መስፈርቱን ያላሟሉ ሆነው በመገኘታቸው ምርቱ ከገበያ ላይ እንዲሰበሰብና አምራቾቹ የችግሩን መንስኤ ለባለስልጣኑ እንዲያቀርቡና የአመራረት ሒደታቸው እንዲያስተካክሉ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች የባለስልጣኑ የምግብ ተቋማት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በትረ ጌታሁን፣ የባለስልጣኑ የመድሃኒት ተቋማት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ገነቴ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ፎቶግራፍ:- አቶ አበራ ደነቀ፣ አቶጌታቸው ገነቴ፣ አቶ በትረ ጌታሁን

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top