Connect with us

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ ነው
Ethiopian News Agency

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

አቶ ማሞ ለኢዜአ እንዳሉት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪው ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 60 በመቶ ተቀማጭ በመሰብሰብ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛልም ነው ያሉት።

የባንኩን አሰራር የበለጠ ለማሻሻልና የኢኮኖሚውን ዕድገት ለማሳለጥ አደረጃጀቱ ጥናት ተደርጎበት ሊቀየር መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ማሞ ገለጻ በ2012 ዓ.ም አብዛኞቹ ባንኮች የጥሬ ብር እጥረት አጋጥሟቸዋል።

የገንዘብ ኖቶች ቅያሬውን ተከትሎ በርካታ ገንዘብ ወደ ባንክ መሰብሰብ በመቻሉ ለኢኮኖሚው የሚሰጠው ብድር ከፍ ማለቱንም አንስተዋል።

በተያዘው ዓመት የባንኮችን ተቀማጭ ገንዘብ በ24 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱንና ለኢኮኖሚው 25 በመቶ ያደገ ብድር ለማሰራጨት መታቀዱን ጠቅሰው፣ ይህን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን ይናገራሉ።

ባለፈው ዓመት ባንኮች ለኢኮኖሚው ካሰራጩት 271 ቢሊዮን ብር 70 በመቶው ለግል ዘርፍ የተሰጠ ነው።(ENA)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top