Connect with us

የመድሀኒት ህጋዊነት ማረጋገጫ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

የመድሀኒት ህጋዊነት ማረጋገጫ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

የመድሀኒት ህጋዊነት ማረጋገጫ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

የመድሀኒት ህጋዊነት ማረጋገጫ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ጋር በመተባበር የመድሀኒት ህጋዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት በሒልተን ሆቴል አስመረቀ።

“i – Verify” የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ መድሀኒት ከአምራቹ አንስቶ እስከ ተጠቃሚው  እስኪደርስ ድረስ ያለውን መረጃ የያዘ ሲሆን የአንድን መድሀኒት ትክክለኛነት፣ የመጠቀሚያ ጊዜው ማለፍ/አለማለፉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።

መተግበሪያውን ከጎግል ኘሌይ ስቶር በማውረድ በቀጥታ የመድሀኒቱን ስም በመፃፍ ወይንም መድሀኒቱን ስም ስካን በማድረግ ህጋዊነቱን ማረጋገጥ እንደሚቻልና በመተግበሪያ ውስጥ መድሀኒቱ ካልተገኘ በዚያው መተግበሪያ ለባለስልጣኑ ሪፖርት ለማድረግ ያስችላል ተብሏል። ይህም የባለስልጣኑን የቁጥጥር አቅም ያሳድጋል ለማሳደግ እንደሚረዳ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ተገልጷል።

አኘልኬሽኑ እኤአ ከኦክቶበር 2020 ጀምሮ በዋንኛነት በመድሀኒት አስመጪና አከፋፋይነት የተሰማሩ ወገኖች እንዲሁም የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ መድሀኒት አምራቾችና አቅራቢ ድርጅቶች፣  የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲጠቀሙበት በሚያስችል መልክ በስራ ላይ ውሏል።

በአኘልኬሽን ማስጀመሪያ የምረቃ ስነስርአት ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሸርላ አብዱላሂ፣ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሄራን ገርባ እንዲሁም ሚስተር ጅም ዶብሰን ዩኤስኤይድ ኢትዮጵያ  ምክትል ዳይሬክተር እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ የምግብና የመድሀኒት ባለስልጣን የአሰራር ስርአቱን በማዘመን ተገልጋዮች የአስመጪነት ፈቃድ ለማግኘት ባሉበት ቦታ ሆነው ከወረቀት ነፃ (Online) አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑም ተጠቅሷል። 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top