Connect with us

” የእንካ ሰላምታ ፖለቲካ….”

" የእንካ ሰላምታ ፖለቲካ…."
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

” የእንካ ሰላምታ ፖለቲካ….”

” የእንካ ሰላምታ ፖለቲካ….”

(እስክንድር ከበደ)

በአንድ የፖለቲካ ውዝግብ ሰሞን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር  መለስ ዜናዊ እየተቆጡ ይናገራሉ፡፡ ከምርጫ በኃላ በርካታ የፖለቲካ መሪዎች ታስረዋል፡፡ 

ፖለቲከኞችን ያስጠነቅቁ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ይሄ “የህጻን ጨዋታ ነው!” በማለት ገሰጹ ፡፡ በአብዛኛው ቤተሰብ አንድ ቴሌቪዥን የሚመለከቱ በመሆኑ፤ የሀገሪቱ ቁንጮ መሪ የህጻን ጨዋታን አንኳሰው መናጋራቸውን አላስተዋሉትም፡፡ ጨዋታ በልጆች እድገት ውስጥ ያለውን የሥነልቦና አካል እድገት ፤በትምህርትና ክህሎት ያለውን እንተወው፡፡ ይህንን የሰማው ወዳጄ ተሾመ ሽብሩ በዛ ዘመን ሲአርዲኤ  ይሰራ ነበር፡፡ 

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከሰስ አለባቸው!”ብሎ ያነሳው ሀሳብ ብዙዎቹ  “አብደሃል እንዴʔ” እንዳሉት ነግሮኝ ነበር፡፡ ብዙዎቻችን ስለ ሰው ልጆች ሰብአዊ መብቶች በተለይ  የህጻናት መብቶች እንደ መብት የማየት ባህል አላዳበረንም፡፡ የልጆችን መብቶች ጠንቅቆ የሚረዳና በሁሉም ድርጊቱ ንግግሩን ጨምሮ ጥንቃቄ የሚያደርግ ማህበረሰብ የሰለጠነ ማህበረሰብ ነው፡፡ ለልጆች ትኩረት የሚሠጥ መሪ ፍቅሩን መልሶ ያገኘዋል፡፡

በሀገራችን መድረክ ላይ ወጥተው ባገኙት አጋጣሚ ስለልጆች በማውራትና ትኩረት እንዲያገኙ  ሀሳባቸውን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቀዳሚዎቹ ይሻላሉ፡፤ ልጆች ነገ ይመርጡኛል ብለው ሳይሆን ሀገር ሀገር የምትሆነው ዛሬ  በልጆች ላይ መስራት እንደሚያዋጣ ስለገባቸው ይመስለኛል፡፡

አንድ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ሲያወያዩ አንድ መምህር ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት የልጁን ፊደል  መልእክት እንዲህ ነበር ያስተላለፈው፡፡

“ፊደል የሚባል የ5 አመት ልጅ አለኝ፡፡ ፊደል ዶክተር አብይ ጋ ልሄድ ስለሆነ ምን ልበልልህ አልኩት”

ለአባቱ  “ፊደል ይወዶታል….ያጨበጭብሎታል በላቸው” አለ የ5 አመቱ ህጻን፡፡

” ይህንን መወደድ እንዴት ይጠቀሙበታልʔ” ብሎ ነበር፡፡

ልጆቹ መደመርን አንብበው ሳይሆን እሳቸው የሚያደርጉት ለልጆች በሚገባቸው መንገድ ነው፡፡ ምናልባት ጥናት ቢካሄድ ከቀደሙት መሪዎች የአብይ አህመድን ስም ሳይሳሳቱ የሚናገሩ ብዙ ህጻናት እናገኛለን፡፡

በእንጦጦ ፓርክ ከተሰሩት አንዱ አስደሳች ነገሮች የህጻናት መጫወቻ ስፍራ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህጻናት መጫወቻ ላይ ሆነው  ሲጫወቱ ታዩ ፡፡ ይህ ድርጊት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ በቴሌቪዥን ላይ የታዩትን በመተቸት ሰውን የሚያሳስቱ ሚዲያዎች/ግለሰቦች ብዙ ናቸው፡፡

እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደ ልጅ መጫወት “ከኮስታራዎቹ መሪዎች ” ጋር አነጻጽሮ ለመተቸት ብዙ ባዘነ፡፡ የልጁን ከፕላስቲክ የተሰራ መናኛ መጫወቻ  እንደ መርጃ ማሳሪያ ተጠቅሞ ያንን ዘመናዊ የልጆች መጫወቻና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማጣጣል የሄደበት መንገድ  ያስጠላል፡፡ 

በተለይ ስህተታቸውን አግዝፎ ሊተቻቸው መሞከሩ ይገርማል፡፡ የልጄ መጫወቻ መሰለኝ ብሎ ለማንጓጠጥ ሞከረ፡፡ ያ ድርጊት ለእሱ ሳይሆን የሆነው ለልጆች ለእሱ ልጅ ነበር፡፡ ልጄ አይታ አልወደደችውም ቢል መልካም፤ የልጅ ጨዋታን እንደተራ የሚወስድ ሰው በቀጣይ የሚደግመው ይህንኑ አተያይ የያዘ ትውልድ መሆኑ አይካድም፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋነኛ ግብ አዋቂዎቹን ሳይሆን  ልጆቹን ነው፡፡ ልጆቹን ከሆነ ደግሞ ተጫውተው ማሳየታቸው ምኑ ነው ጥፋታቸውʔ እንደ ልጅ ተጫወቱ ብሎ ደጋግሞ መሪውን ሲወርፍ ፤ ከእራሱ ልጅ ጨምሮ በልጆች ላይ የሚያፌዝ መሆኑን አልተረዳውም፡፡ 

በርካታ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ይጫወታሉ ይህ ደግሞ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ  ከሳኡዲ አረቢያ ሲመለሱ በሚሊኒየም አዳራሽ ባደረጉት ንግግር ልጆችና ታዳጊዎች የመዝናኛ ስፍራ ያስፈልጋቸዋል ማለታቸው ይታወሳል፡፡ 

ልጆች ቦርቀውና ተጫውተው ካላወቁ በወጣትነታቸው በድንጋይ መጫወት ይመጣል ፤በተገቢው እድሜ ተጫውተው እንዲያድጉ ሊሰራ ይገባል ብለው ነበር፡፡ ያንን ቃል በተወሰነ መልኩ የሚያንጸባርቅ ስራ ሰርተዋል፡፡

ከህዝብ ብዛታችን የላቀውን ድርሻ የያዙትን ልጆችን  የምታከበር ፤ ለሥነ ልቦና አካላዊ ጤና እድገታቸው አብዝታ የምትጨነቅ ሀገር ስትሆን ዛሬ  እንደ ቁማር መወዳደሪያ  “አትፈርስም ፤ትፈርሳለች ” …..”አሀዳዊ ፤ፌደራሊስት” እያልን ሚዲያውን ሁሉ በእንካ ሰላምታ ፖለቲካም አየሩን አይበክልም ነበር ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top