Connect with us

የሐዘን_መግለጫ

የሐዘን_መግለጫ
አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት

ዜና

የሐዘን_መግለጫ

የሐዘን_መግለጫ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትላንት አመሻሽ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  በደረሰው እሳት አደጋ በጠፋው የሰው ህይወት እና በወደመው ንብረት ማዘኑንን ገለጸ፡፡

በትላንናው ዕለት ከምሽቱ 1:30 ሰዓት አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል  አየርአምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባሉ መኖሪያ ቤቶች  ላይ በደረሰው  የእሳት አደጋ  የአራት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአንድ ሰው  ላይ ከባድ የቃጠሎ አደጋ ደርሷል፡፡

የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት  በአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና  አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ ሰራተኞች  በቁጥጥር ስር መዋሉን የቦሌ ክፍለ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጉልላት ከበደ ገልጸዋል፡፡

የአደጋውን መንስዔ እና በንብረት ላይ  የደረሰውን ውድመት በተመለከተ ፖሊስ  እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት  በማጣራት ላይ መሆናቸውን  አቶ ጉልላት ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለጠፋው የሰው ህይወት እና ለደረሰው አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።

(አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top