Connect with us

በመዲናዋ የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች የጣምራ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ …

በመዲናዋ የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የጣምራ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ አሰራር ሊዘረጋ ይችላል ተባለ
Photo: Social Media

ዜና

በመዲናዋ የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች የጣምራ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ …

በመዲናዋ የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የጣምራ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ አሰራር ሊዘረጋ ይችላል ተባለ

በአዲሰ አበባ ከተማ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የተለያዮ እቅዶችን አቅዶ ወደ ተግባር ለመግባት ከሚመለከታቸወ አካላት ጋር እየተወያየ መሆኑን የከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የከተማዋን የትራፊክ እንቅሰቃሴ የተሻለ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን በመከወን ላይ እንደሚገኝ ነው የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ጅሬኛ ሄርጳ ለፋና ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።

በዚህም የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የጣምራ ማለትም 3 ሰው እና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው አሸከርካሪዎች የጣምራ ትራንሰፖርት ካልሰጡ ጠዋት ከ1 እሰከ 3 ሰዓት እና ምሸት ከ11 እሰከ ምሽት 1 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ተናግረዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top