Connect with us

አንድነት ኢንተርናሽናል  እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ታገዱ

አንድነት ኢንተርናሽናል  እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ታገዱ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

አንድነት ኢንተርናሽናል  እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ታገዱ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር  ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች  ለግዜው መታገዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች   አንድነት ኢንተርናሽናል  እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡

በትምህርት ቤቶቹ ላይ  ውሳኔ የተላለፈው  ትምህርት ቤቶቹ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡

ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት( ትምህርት ሚኒስቴር) ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥኖ ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ትምህርት ቤቶቹ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ መታገዳቸውን ተገልጿል፡፡(ኢኘድ)

 

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top