Connect with us

የምርጫ ቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ሀላፊነታቸውን ለቀቁ

የምርጫ ቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ሀላፊነታቸውን ለቀቁ
Photo: Social Media

ዜና

የምርጫ ቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ሀላፊነታቸውን ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን ተሰማ።
ቦርዱ በይፋዊ ድረገፁ የአባሉን መልቀቂያ ማስገባት ከማሳወቅ ባለፈ ያሰፈረው ዝርዝር ዘገባ የለም።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 7 ቀን 2011 ባካሄደው ስብሰባ አዋጅ 1133/2011 መሠረት ከሾማቸው አራት ተጨማሪ የቦርድ አባላት መካከል ዶ/ር ጌታሁን አንዱ ነበሩ። የቦርድ አባላቱ ምልመላ ሂደትን ለማስተባበር ሰባት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት መልማይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል።

በዚህ መሠረትም መልማይ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ዕጩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት መልማይ ኮሚቴ የውስጥ አሰራር መመሪያ በማውጣት፣ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ቦርድ አባልነት ጥቆማ ሂደት ከሃያ በላይ በሚሆኑ የመገናኛ አውታሮች ለሕዝብ እንዲገለፅ በማድረግ፣ 200 ጥቆማዎች በስልክ፣ በኢ-ሜይል፣ በአካል እና ፋክስ አማካኝነት ተቀብሏል፡፡ የቀረቡት 200 ተጠቋሚዎችም በሦስት የማጣሪያ ምዕራፎች እንዲያልፉ በማድረግ ለሹመት መብቃቸው ይታወሳል።

ዶክተር ጌታሁን ካሳ በሕግ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በትግራይ ክልል አቃቤ ህግነት፣ በመቀሌ ዪኒቨርሲቲ በመምህርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ ቢሮዎች በአማካሪነት፣ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት (DFID, CAFOD, UNG international የመሳሰሉት)፣ ኢምባሲዎች እና የመንግሥት ተቋማት በአማካሪነት፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡ ከህግ ባለሞያነታቸው፣ አማካሪነታቸው እና መምህርነታቸው በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር በሚገኘው የሕግ እና የፍትህ ጉዳዮች ማሻሻያ አማካሪ ጉባኤ ውስጥ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር ጌታሁን የትግርኛ አማርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ናቸው፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top