Connect with us

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቅ

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመስከረም 25 በኋላ “መንግስት የለም” በሚል አገራዊ ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ ርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቅ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቅ

ፌዴራል ፖሊስ ከመስከረም 25 በኋላ “ህጋዊ መንግስት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር የሚጥሩ ሃይሎችን እንደማይታገስ ገለጸ

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመስከረም 25 በኋላ “ህጋዊ መንግስት የለም” በሚል አገራዊ ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመስድ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ የደመራና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወኑ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅትን እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።

የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት የጠቆሙት ኮሚሽነር ጀነራሉ፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ፣ ገላንና ሰበታ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በበዓሉ ለመታደም የሚመጡ ምዕምናንና እንግዶች የይለፍ ባጅ ማድርጋቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ይህን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ ፖሊስ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ተመሳሳይ የይለፍ ባጅ አሰርተው ለመግባት የሚሞክሩ አካላት መለየት የሚያስችል አሰራር ስላለ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አሰተላልፈዋል።

የዘንድሮው መስቀል እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ፓሊስ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።
በዓላቱን ተገን አድርገው ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስን ማንኛውንም አካል ፖሊስ አይታገስም ብለዋል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ አክለውም ከመስከረም 25 በኋላ “መንግስት የለም” በሚል አገራዊ ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ህዝቡን ለአመፅ እንዲነሳሳ የሚያደርጉ መልዕክቶችን በስፋት የሚያሰረጩ አካላት እንዳሉ ጠቅሰው እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው።

በባአሉም ይሁ በሌላ አጋጣሚ ህብረተሰቡ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲመለከት የተለመደ ትብብሩንና ጥቆማውን ለፖሊስ እንዲያደርስም ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top