Connect with us

ፖሊስ ልደቱ አያሌውን ለመልቀቅ ማንገራገሩ አነጋገረ

ፖሊስ ልደቱ አያሌውን ለመልቀቅ ማንገራገሩ አነጋገረ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ፖሊስ ልደቱ አያሌውን ለመልቀቅ ማንገራገሩ አነጋገረ

የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በአንድ መቶ ሺ ዋስ እንዲለቀቁ በትላንትናው ዕለት መወሰኑ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለት የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመያዝ አቶ ልደቱን ለማስፈታት የትግል አጋሮቻቸው ያደረጉት ጥረት የገጠውን ሳንካ በሚመለከት አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ሊቀመንበር በፌቡ ገፃቸው የሚከተለውን አስፍረዋል።
***

“…የአቶ ልደቱን የማስፈቻ ትእዛዝ ይዘን የቢሾፍቱ ከተማ መምሪያ የተገኘነው በጠዋት ነበር። ማስፈቻውን ይዘን መርማሪውን ስናናግረው አስደንጋጭ መልስ መለሰልን። አቶ ልደቱ እኛ ጋር ያለው በአደራ ነው ስለዚህ እሱን የመፍታት ስልጣን የለኝም። አዳማ ምስራቅ ሸዋ ፍትህ ቢሮ ሂዱና ይፈታ ብለው ፓራፍ ያድርጉበት አሉን። ነገሩ ስላልጣመን ይሄን ማለታችሁን በደብዳቤ ግለፁና ስጡን ስንል ይሄ የተለመደ አሰራር ነው አቶ ልደቱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም በአደራ ተቀምጠዋል በሚል ጥያቄያችንን ውድቅ አደረገብን። እኛም ወደ አዳማ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ዘንድ ቀርበን ጉዳዩን አስረዳን። ከፍርድ ቤት በላይ አይደለንም። ትእዛዙ የተፃፈለት አካል ነው ትእዛዙን መፈፀም ያለበት ብለው እየሳቁ ሸኙን። እያዘንን ወደ ቢሾፍቱ መምሪያ ተመልሰን የተባልነውን ለመምሪያ ሃላፊውን ነገርነው። ሃላፊው ለምን ሄዳችሁ መሄድ አልነበረባችሁም ካለ በዃላ ከኛ አቅም በላይ ነው የሚመለከታቸው አካላት እየመጡ ነው ከሰአት ተነጋግረን እንወስናለን አለን።…”

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top