Connect with us

የእነ-እስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ!

የእነ-እስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ!
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

የእነ-እስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ!

የእነ-እስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ!

#ከችሎት በፊት ጊቢ ውስጥ ፦

እነ እስክንድር ከፊትና ከኋላ በከፍተኛ አጀብ ታጅበው ተሳፍረው ከመጡበት መኪና ሲውርዱ ፤ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር እና አባላት ፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም የእስረኞች ቤተሰብ አስቀድመው በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይጠባበቋቸው ስለነበር የተደረገላቸው አቀባበል ደማቅ ከመሆኑ ባሻገር ለታሳሪዎች ብርታትን የሚሰጥ ነበር ።

እነ እስክንድር ከመኪና ወርደው የእስረኞች ማረፊያ ወደ ሆነው በሽቦ የታጠረ ክፍል እንዲሄዱ ሲደረግ ፤ ችሎት ለመታደም የመጣውን ሰው ቁጣ በተቀላቀለበት ዛቻና ማስፈራሪያ የፖሊስ አዛዥ የሆነ በእጅ የሬዲዮ መገናኛ የያዘ ” ማንም ሰው በእጁ ስልኩን ይዞ ፎቶ ለማንሳት ቢሞክር ……. ” በማለት ማስጠንቀቂያ እየሰጠ “ሁላችሁም ወደ ጥግ ሂዱ አርፋቹ ተቀመጡ ፣ አለበለዚያ ጠራርገን ነው የምናስወጣቹ ” በማለት ትዕዛዝ አስከባሪ ለሆኑ መሳሪያ ታጣቂዎች በምልክት ትዕዛዝ ሰጥቶ ፤ በአካባቢው ሲንጎማለል ለሚመለከተው ሰው በከፍተኛ ጦር ግንባር ግዳጁን የጠለ ወንድ የሆነ ጀግና ይመስል ነበር።

ከደቂቃዎች ቆይታ በኋላ እነ-እስክንድር በጓሮ በር ወደ ችሎት እንዲገቡ ተደረገ ። በመቀጠል ጋዜጠኞች እና ጠበቆች ተፈትሸው ገቡ ፤ ከአፍታ ቆይታ በኋላ ጠበቃ ሄኖክ ከችሎት በመውጣት የአምስት ሰዎችን ስም በመጥራት ለፖሊስ አዛዥ በመንገር ወደ ውስጥ ገባ ፤ አምስት ሰዎች ጥብቅ ፍተሻ ተደርጎላቸዉ በችሎት እንዲታደሙ ተደረገ።

ቁጥሩ ብዛት ያለው ሰው ከችሎት አዳራሽ ውጪ መጨረሻውን ለማየት እና ለመስማት የእንግዶች ማረፊያ ቦታ ተቀምጠዋል ።

#ከችሎት በፊት አዳራሹ ውስጥ ፦

የዕለቱ ችሎች ከመዋሉ በፊት ፤ በዓይን ጥቅሻ እና በእጅ መልዕክት እነ እስክንድር እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የትግል አጋሮቻቸው የወደጅነት ሰላምታ ተለዋውጠዋል። በእነ እስክንድር ላይ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬ በደንብ ይታይባቸዋል ፤ ለሁሉም ሰላምታ ሲሰጡ ፊታቸው ላይ ብርታት፣ጽናት ልባዊ የሆነ ውስጣዊ ፍቅርና ፈገግታ አልተለያቸውም ።

#የእለቱ ችሎት ፦

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት አቃቤ ህግ ከዚህ በፊት የመሰረተው ክስ ዋስትና ላይ ዝርዝር ክሱን ተመልክቶ ውሳኔ ለማሳረፍ ቀጠሮ የተሰጠበት መዝገብ እንደሆነ የእለቱ የመሐል ዳኝ የገለፁ ሲሆን ።

አያይዘውም ፤ የዋስትና ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሦስት መሰረታዊ ነገር መሟላት አለበት በማለት ፦ ” በሰኔ 23 እና ሰኔ 24 2012 ዓ.ም በሰው ላይም በንብረት ላይም ደረሰ የተባለው ጉዳት ተለይቶ እንዲቀርብ፣ የደረሰው ጉዳት ቦታው የት እንደሆነ፣ በየት ክፍለ ከተማ እና ወረዳ፣ በስንት ሰዓት የሚለው መገለፅ አለበት ያለው ፍርድ ቤቱ፤ ቦታው ከታወቀ በኋላም የተከሳሾቹ የወንጀል ተሳትፎ በዝርዝር ተለይቶ” ያልቀረበ በመሆኑ በቀረበው የዋስትና መዝገብ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ያልተቻለ በመሆኑ ፤

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ግለሰቦች ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል እና ለመስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት በችሎት እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ አዟል።

#በችሎት የተሰሙ አቤቱታ ፦

ማረሚያ ቤት ከቤተሰብ ጋር እያገናኛቸው እንዳልሆነ፣ ምግብና ልብስም እየገባላቸው እንዳልሆነ ፤ የህክምና አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነ አቤቱታ ሁሉም ያቀረቡ ሲሆን ፤ ፍርድ ቤቱም ” ጊዜ የማይሰጡ የህክምና እና በቤተሰብ መጎብኘት መብቶች መከበር ያለበት በመሆኑ ” ማረሚያ ቤቱ እንዲፈፅም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።

በተናጥል የቀረበ አቤቱታ እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና ምላሽ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ እመለስበታለው ……(ይድነቃቸው ከበደ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top