Connect with us

የአዲስ ዓመት ሰርኘራይዝ!

የአዲስ ዓመት ሰርኘራይዝ!
Addis Ababa. Photograph: Charlie Rosse

ዜና

የአዲስ ዓመት ሰርኘራይዝ!

የአዲስ ዓመት ሰርኘራይዝ!

የአዲስአበባ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህክምና ለሚከታታሉ ዜጎች ወጪያቸውን ሊሸፍን ነው
—————-
በ2013 ዓ.ም መንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህክምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጫቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ የዘውድቱ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያን ጎብኝተዋል።

በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህከምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጫቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ፣ መንግስት ችግሩን ተረድቶ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

ህሙማኑ በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት በማድረግ ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ መሆኑ ይታወቃል።

በአሁኑ ወቅት በሶስት የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በሚኒሊክ፣ ዘውዲቱና ጳውሎስ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

በእነዚህ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት እያደረጉ ላሉ ዜጎች በ2013 ዓ.ም አመቱን ሙሉ ወጫቸው እንደሚሸፈን ምክትል ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።

ምክትል ከንቲባዋ የምስጋና ቀንን አስመልክተው በዘውድቱ ሆስፒታል ያለውን የህክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች የለይቶ ማቆያ ጎብኝተዋል።

ጳጉሜን 1 የይቅርታ ቀን፣ ጳጉሜን 2 የአብሮነት፣ ጳጉሜን 3 የአምባሰደርነት፣ ጳጉሜን 4 የምስጋና እንዲሁም ጳጉሜን 5 ቀን የብሩህ ተስፋ ብስራት ቀን በሚል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየታሰበ ይገኛል።

(ምንጭ፡-ኢዜአ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top